Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 15:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 መዘ​ም​ራ​ንም ኤማ​ንና አሳፍ ኤታ​ንም በናስ ጸና​ጽል ከፍ አድ​ር​ገው ያሰሙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 መዘምራኑ ኤማን፣ አሳፍና ኤታን በናስ ጸናጽል ድምፁን ከፍ አድርገው እንዲያሰሙ ተሾሙ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 መዘምራንም የነበሩት ኤማንና አሳፍ ኤታምንም የናሱን ጸናጽል ድምፅ ከፍ አድርገው ያሰሙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 መዘምራንም ኤማን አሳፍና ኤታን በናስ ጸናጽል ከፍ አድርገው ያሰሙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 15:19
13 Referencias Cruzadas  

ከሰ​ዎ​ችም ሁሉ ይልቅ ብልህ ነበረ፤ ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው ከኤ​ታ​ንና ከማ​ሖል ልጆች ከአ​ው​ና​ንና ከከ​ል​ቀድ፥ ከደ​ራ​ልም ይልቅ ጥበ​በኛ ነበረ። በዙ​ሪ​ያ​ውም ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ዝናው ወጣ።


ዳዊ​ትና እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከመ​ዘ​ም​ራን ጋር በበ​ገና፥ በመ​ሰ​ን​ቆና በከ​በሮ፥ በጸ​ና​ጽ​ልና በመ​ለ​ከት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሙሉ ኀይ​ላ​ቸው ይዘ​ምሩ ነበር።


ዳዊ​ትም በዜማ ዕቃ፥ በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በጸ​ና​ጽ​ልም እን​ዲ​ያ​ዜሙ፥ ድም​ፃ​ቸ​ው​ንም በደ​ስታ ከፍ እን​ዲ​ያ​ደ​ርጉ መዘ​ም​ራ​ኑን “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ሹሙ” ብሎ ለሌ​ዋ​ው​ያን አለ​ቆች ተና​ገረ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር በሁ​ለ​ተ​ኛው ተራ የሆ​ኑ​ትን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ዘካ​ር​ያ​ስን፥ ቤንን፥ አዝ​ኤ​ልን፥ ስሜ​ራ​ሞ​ትን፥ ኢያ​ሄ​ልን፥ ኡኒን፥ ኤል​ያ​ብን፥ በና​እ​ያን፥ መዕ​ሤ​ያን፥ መታ​ት​ያን፥ ኤል​ፋ​ይን፥ ሜቄ​ድ​ያን፥ በረ​ኞ​ች​ንም አብ​ዲ​ዶ​ምን፥ ኢያ​ኤ​ል​ንና ዖዝ​ያ​ስን አቆሙ።


ዘካ​ር​ያስ፥ አዝ​ኤል፥ ሰሚ​ራ​ሞት፥ ኢያ​ሔል፥ ዑኒ፥ ኤል​ያብ፥ መዕ​ሤያ፥ በና​ያስ በመ​ሰ​ንቆ በል​ዑል ቃል ያዜሙ ነበር።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ካህ​ናቱ ከፍ አድ​ር​ገው ለማ​ሰ​ማት መለ​ከ​ትና ጸና​ጽል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መዝ​ሙ​ራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤ​ዶ​ታም ልጆች ግን በረ​ኞች ነበሩ።


አለ​ቃ​ውም አሳፍ ነበረ፤ ከእ​ር​ሱም ቀጥሎ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢያ​ሔል፥ ሰሜ​ራ​ሞት፥ ይሔ​ኤል፥ ማታ​ትያ፥ ኤል​ያብ፥ በና​ያስ፥ አብ​ዲ​ዶም፥ ይዒ​ኤል በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ አሳ​ፍም በጸ​ና​ጽል ይዘ​ምሩ ነበር።


ዳዊ​ትና የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆ​ችም ከአ​ሳ​ፍና ከኤ​ማን ከኤ​ዶ​ት​ምም ልጆች በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በጸ​ና​ጽ​ልም የሚ​ዘ​ምሩ ሰዎ​ችን ለማ​ገ​ል​ገል ለዩ፤ በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውም ሥራ የሚ​ሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።


እነ​ዚህ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በጸ​ና​ጽ​ልና በበ​ገና፥ በመ​ሰ​ን​ቆም ከአ​ባ​ታ​ቸው ጋራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለማ​ገ​ል​ገል ወደ ንጉሡ ቀር​በው ያመ​ሰ​ግኑ ነበር። አሳ​ፍም ኤዶ​ት​ምም ኤማ​ንም ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።


ሌዋ​ው​ያ​ንም፥ ከቀ​ዓት ልጆ​ችና ከቆሬ ልጆች የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከፍ ባለ ታላቅ ድምፅ ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ቆሙ።


ካህ​ና​ቱም በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ሌዋ​ው​ያ​ኑም ደግሞ፥ “ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” የሚ​ለ​ውን የዳ​ዊ​ትን መዝ​ሙር እየ​ዘ​መሩ፥ ንጉሡ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​መ​ስ​ገን የሠ​ራ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህ​ና​ቱም በፊ​ታ​ቸው መለ​ከት ይነፉ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ቆመው ነበር።


ድምፁ መል​ካም በሆነ ጸና​ጽል አመ​ስ​ግ​ኑት፤ በጸ​ና​ጽ​ልና በእ​ል​ልታ አመ​ስ​ግ​ኑት።


ለድ​ሆ​ችና ለድሃ አደ​ጎች ፍረዱ፤ ለተ​ገ​ፋ​ውና ለም​ስ​ኪኑ ጽድ​ቅን አድ​ርጉ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos