Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 15:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 መዘምራንም የነበሩት ኤማንና አሳፍ ኤታምንም የናሱን ጸናጽል ድምፅ ከፍ አድርገው ያሰሙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 መዘምራኑ ኤማን፣ አሳፍና ኤታን በናስ ጸናጽል ድምፁን ከፍ አድርገው እንዲያሰሙ ተሾሙ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 መዘ​ም​ራ​ንም ኤማ​ንና አሳፍ ኤታ​ንም በናስ ጸና​ጽል ከፍ አድ​ር​ገው ያሰሙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 መዘምራንም ኤማን አሳፍና ኤታን በናስ ጸናጽል ከፍ አድርገው ያሰሙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 15:19
13 Referencias Cruzadas  

እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና በመሰንቆም እንዲዘምሩ፥ በእግዚአብሔርም ቤት እንዲያገለግሉ ከአባታቸው ትእዛዝ በታች ነበሩ፤ አሳፍም ኤዶታምም ኤማንም ከንጉሡ ትእዛዝ በታች ነበሩ።


ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አወድሱት፥ ድምፁ በሚሰማ ጸናጽል አወድሱት።


ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶታም ልጆች በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም ትንቢት የሚናገሩትን ሰዎች ለማገልገል ለዩ፤ በአገልግሎታቸውም ሥራ ይሠሩ የነበሩት ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።


ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ከፍ አድርገው ለማሰማት መለከትና ጸናጽል ለእግዚአብሔርም መዝሙራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤዶታምም ልጆች ጠባቂዎች ነበሩ።


አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም ቀጥሎ መሰንቆና በገና ይጫወቱ የነበሩት ዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድ-ኤዶም፥ ይዒኤል ነበሩ፤ አሳፍም የጸናጽልን ድምፅ ያሰማ ነበረ።


ዳዊትም በዜማ ዕቃ በመሰንቆና በበገና በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን ወንድሞቻቸውን እንዲሾሙ ለሌዋውያን አለቆች ተናገረ።


ዳዊትና እስራኤል ሁሉ በዝማሬና በበገና በመሰንቆና በከበሮ በጸናጸልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ያሸበሽቡ ነበር።


እርሱ ከሰዎች ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ጥበበኛ ነበረ። ከኤዝራሐዊው ኤታን፥ የማሖል ልጆች ከሆኑት ከሄማን፥ ከካልኮልና ከዳርዓዕ የሚበልጥ ጥበበኛ ነበረ፤ ዝናውም ከፍ ብሎ በጐረቤት ሕዝቦች ሁሉ ዘንድ አስተጋባ።


ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ደረጃ ያሉትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ ያዝኤልን፥ ሰሚራሞትን፥ ይሒኤልን፥ ዑኒን፥ ኤልያብን፥ በናያስን፥ መዕሤያን፥ መቲትያን፥ ኤሊፍሌሁን፥ ሚቅኔያን፥ ደጁንም የሚጠብቁትን ዖቤድ-ኤዶምንና ይዒኤልን ሾሙ።


ዘካርያስ፥ ዓዝዔል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ ዑኒ፥ ኤልያብ፥ መዕሤያ፥ በናያስ በመሰንቆ ምሥጢር ነገር ያዜሙ ነበር።


ካህናቱም በየሥርዓታቸው፥ ሌዋውያኑም ደግሞ፦ ጽኑ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና ጌታን አመስግኑ የሚለውን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ፥ ንጉሡ ዳዊት ጌታን ለማመስገን የሠራውን የጌታን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህናቱም በፊታቸው መለከት ይነፉ ነበር፤ እስራኤልም ሁሉ ቆመው ነበር።


ሌዋውያንም፥ የቀዓት ልጆችና የቆሬ ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ ጌታን እጅግ ታላቅ በሆነ ድምፅ ሊያመሰግኑት ቆሙ።


ዝማሬውን አንሡ ከበሮንም ስጡ፥ ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios