እግዚአብሔርን በተቀደሱ ቦታዎች አመስግኑት፤ በኀይሉ ጽናት አመስግኑት።
ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በታላቅ ጠፈሩ አመስግኑት።
ሃሌ ሉያ። ጌታን በመቅደሱ አወድሱት፥ በኃይሉ ጠፈር አወድሱት።
እግዚአብሔርን አመስግኑ! እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት! የሚያስደንቅ ኀይሉ ባለበት በሰማይ አመስግኑት!
እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ፥ በመንግሥቱም ሁሉን ይገዛል።
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ፥ በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ።
እግዚአብሔርን አዲስ ምስጋናን አመስግኑት፤ ምስጋናውም በጻድቃኑ ጉባኤ ነው።
በመከራህ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ፤ የያዕቆብ አምላክ ስምም ይቁምልህ።
ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልህ፥ ከጽዮንም ይቀበልህ።
ወደ ጥፋት ብወርድ በደሜ ምን ጥቅም አለ? አፈር ያመሰግንሃልን? ጽድቅህንም ይናገራልን?
እኔም አየሁ፤ እነሆም በኪሩቤል ራስ ላይ ባለው ጠፈር በላያቸው እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ ዙፋን የሚመስል መልክ ተገለጠ።