አራዊትም ሁሉ በየወገናቸው፥ እንስሳትም ሁሉ በየወገናቸው፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾችም ሁሉ በየወገናቸው፥ ወፎችም ሁሉ በየወገናቸው፥ የሚበሩ ወፎችም ሁሉ፥
መዝሙር 148:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አራዊትም፥ እንስሳትም ሁሉ፥ ተንቀሳቃሾችም፥ የሚበርሩ ወፎችም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት ሁሉ፣ በምድር የሚሳቡ ፍጥረታትና የሚበርሩ ወፎችም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አራዊትና እንስሳት ሁሉ፥ የሚሳቡና የሚበርሩ ወፎችም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አራዊትና ለማዳ እንስሶች፥ በምድር የምትሳቡና በክንፍ የምትበርሩ ፍጥረቶች ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት። |
አራዊትም ሁሉ በየወገናቸው፥ እንስሳትም ሁሉ በየወገናቸው፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ተንቀሳቃሾችም ሁሉ በየወገናቸው፥ ወፎችም ሁሉ በየወገናቸው፥ የሚበሩ ወፎችም ሁሉ፥
የምድረ በዳ አራዊት፥ ቀበሮችና ሰጎኖች፥ ያከብሩኛል። የመረጥሁትን ሕዝቤን አጠጣ ዘንድ በምድረ በዳ ውኃን፥ በበረሃም ወንዞችን ሰጥቻለሁና፤
ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎችንም ያወጣል፤ ፍሬም ያፈራል፤ ታላቅም ዝግባ ይሆናል፤ በበታቹም ወፎች ሁሉ ያርፋሉ፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርር ሁሉ ይጠጋል፤ ቅርንጫፉም ይሰፋል።