መዝሙር 147:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጽዮንም ሆይ፥ አምላክሽን አመስግኚ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኮአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል፤ ከእስራኤል የተበተኑትን ይሰበስባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ኢየሩሳሌምን ይሠራል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ያድሳል፤ ከእስራኤል የተሰደዱትንም ይመልሳል። |
እንዲህም ሆነ፤ ጠላቶቻችን ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙሪያችን የነበሩ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፤ አይተውም እጅግ ተደናገጡ፤ ይህም ሥራ በአምላካችን እንደ ተፈጸመ አወቁ።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦርም የጠፉ፥ በግብፅ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ይሰግዳሉ።
ከእስራኤል የተበተኑትን የሚሰበስብ ጌታ እግዚአብሔር፦ ወደ ተሰበሰቡት ሌሎችን እሰበስብለታለሁ” ይላል።
አሕዛብ ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩና፥ “እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፤ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል በሉ።
የእስራኤል ድንግል ሆይ እንደ ገና እሠራሻለሁ፤ አንቺም ትሠሪያለሽ፤ እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ትወጫለሽ።
እነሆ በቍጣዬና በመዓቴ፥ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት ሀገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤
ከብዙ ዘመንም በኋላ ትፈለጋለህ፤ በኋለኛውም ዘመን፥ የዘለዓለም ባድማ በነበሩ በእስራኤል ተራሮች ላይ ከብዙ ሕዝብ ውስጥ ወደ ተሰበሰበች፥ ከሰይፍ ወደ ተመለሰች ምድር ትገባለህ፤ እርስዋም ከሕዝብ ውስጥ ወጥታለች፤ ሁሉም በሰላም ይቀመጡበታል።
እግዚአብሔርም ኀጢአትህን ይቅር ይልሃል ይራራልህማል፤ እግዚአብሔርም አንተን ከበተነበት ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መልሶ ይሰበስብሃል።