ሞትን እንሞታለንና፥ በምድርም ላይ እንደ ፈሰሰና እንደማይመለስ ውኃ እንሆናለንና፥ እግዚአብሔርም ነፍስን ይወስዳል። የተጣለውንም ከእርሱ ያርቅ ዘንድ ያስባል።
መዝሙር 144:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የልጅ ልጆች ሥራህን ያደንቃሉ፥ ኀይልህንም ይናገራሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤ ዘመኑም ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው ከንቱን ነገር ይመስላል፥ ዘመኑ እንደ ጥላ ያልፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው እንደ ነፋስ ሽውታ ነው፤ ዘመኑም እንደ ጥላ የሚያልፍ ነው። |
ሞትን እንሞታለንና፥ በምድርም ላይ እንደ ፈሰሰና እንደማይመለስ ውኃ እንሆናለንና፥ እግዚአብሔርም ነፍስን ይወስዳል። የተጣለውንም ከእርሱ ያርቅ ዘንድ ያስባል።
አባቶቻችን ስደተኞች እንደ ነበሩ እኛ በፊትህ ስደተኞችና መጻተኞች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ናት፤ አትጸናምም።
ይልቁንም ከአንድ ዐይነት ጭቃ የተፈጠርን እኛ፥ በተፈጠርንበት የጭቃ ቤት የሚኖሩትን እንደ ብል ይጨፈልቃቸዋል።