Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መክብብ 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሰባ​ኪው፥ “ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከ​ንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው” ይላል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “የከንቱ ከንቱ፤” ይላል ሰባኪው፤ “ሁሉም ነገር ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ ነው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፥ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ጥበበኛው እንዲህ አለ፦ ሁሉ ነገር ከንቱ፥ እንዲያውም የከንቱ ከንቱ ነው፤ ሁሉም ነገር በፍጹም ከንቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፥ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 1:2
23 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን በከ​ንቱ ነገ​ርን የሚ​ፈ​ልግ ሰው፥ ከሴ​ትም የሚ​ወ​ለድ ሟች የሜዳ አህ​ያን ይመ​ስ​ላል።


የልጅ ልጆች ሥራ​ህን ያደ​ን​ቃሉ፥ ኀይ​ል​ህ​ንም ይና​ገ​ራሉ፥


ሕፃ​ን​ነ​ትና ጕብ​ዝና፥ አለ​ማ​ወ​ቅም ከንቱ ናቸ​ውና ከል​ብህ ቍጣን አርቅ፥ ከሰ​ው​ነ​ት​ህም ክፉ ነገ​ርን አስ​ወ​ግድ።


ሰው ብዙ ዘመን በሕ​ይ​ወት ቢኖር፥ በሁ​ሉም ደስ ቢለው፤ የጨ​ለ​ማ​ውን ዘመን ያስብ፥ ብዙ ቀን ይሆ​ና​ልና። የሚ​መ​ጣ​ውም ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።


ሰባ​ኪው አለ፥ “ሁሉ ከንቱ፥ የከ​ንቱ ከንቱ ነው።”


እጄ የሠ​ራ​ቻ​ትን ሥራ​ዬን ሁሉ፥ የደ​ከ​ም​ሁ​በ​ት​ንም ድካ​ሜን ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነበረ፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም ትርፍ አል​ነ​በ​ረም።


እኔም በልቤ፥ “አላ​ዋ​ቂን የሚ​ያ​ገ​ኘው እን​ዲሁ እኔ​ንም ያገ​ኘ​ኛል፤ እኔም ለምን እጅግ ጠቢብ ሆንሁ?” አልሁ፤ የዚ​ያን ጊዜም በልቤ፥ “ይህ ደግሞ ከንቱ ነው” አልሁ፥ አላ​ዋቂ በከ​ንቱ መና​ገ​ርን ያበ​ዛ​ልና።


ከፀ​ሐ​ይም በታች የተ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ በእኔ ላይ ክፉ ነውና ሕይ​ወ​ትን ጠላሁ፥ ሁሉም ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ጠቢብ ወይም አላ​ዋቂ እን​ደ​ሚ​ሆን ከፀ​ሐይ በታ​ችም በደ​ከ​ም​ሁ​በ​ትና ጠቢብ በሆ​ን​ሁ​በት በድ​ካሜ ሁሉ ይሰ​ለ​ጥን እንደ ሆነ የሚ​ያ​ውቅ ሰው ማን ነው? ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።


ሰው በጥ​በ​ብና በዕ​ው​ቀት በብ​ር​ታ​ትም ከደ​ከመ በኋላ ለሌላ ላል​ደ​ከ​መ​በት ሰው ዕድ​ሉን ያወ​ር​ሳ​ልና፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ትል​ቅም መከራ ነው።


ዘመኑ ሁሉ መከራ፥ ቍጣም፥ ቅሚ​ያም ነው፤ ልቡም በሌ​ሊት አይ​ተ​ኛም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።


እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበ​ብ​ንና ዕው​ቀ​ትን፥ ደስ​ታ​ንም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ለኀ​ጢ​አ​ተኛ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እን​ዲ​ሰ​በ​ስ​ብና እን​ዲ​ያ​ከ​ማች ጥረ​ትን ይሰ​ጠ​ዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ብር​ንና ወር​ቅን፥ የከ​በ​ረ​ው​ንም የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንና የአ​ው​ራ​ጆ​ችን መዝ​ገብ ለራሴ ሰበ​ሰ​ብሁ፤ ሴቶ​ችና ወን​ዶች አዝ​ማ​ሪ​ዎ​ችን፥ የሰ​ዎች ልጆ​ች​ንም ተድላ አደ​ረ​ግሁ፤ የወ​ይን ጠጅ ጠማ​ቂ​ዎ​ች​ንና አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ች​ንም አበ​ዛሁ።


ለሰው ልጆች ሞት አለ​ባ​ቸው፥ ለእ​ን​ስ​ሳም ሞት አለ​ባ​ቸው፤ አንድ ሞት አለ​ባ​ቸው፤ አንዱ እን​ደ​ሚ​ሞት ሌላ​ውም እን​ዲሁ ይሞ​ታል፤ ለሁ​ሉም አንድ እስ​ት​ን​ፋስ አላ​ቸው፥ ሰው ከእ​ን​ስሳ ብል​ጫው ምን​ድን ነው? ሁሉም ከንቱ ነውና ምንም የለ​ውም።


ከእ​ርሱ በፊት የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ቍጥር የላ​ቸ​ውም፤ በኋላ የሚ​መ​ጡት ግን በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ቸ​ውም። ይህ ደግሞ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


እኔ ድካ​ምን ሁሉና የብ​ል​ሃት ሥራ​ውን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ ለሰ​ውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ቅን​አ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


አንድ ሰው ብቻ​ውን አለ፥ ሁለ​ተ​ኛም የለ​ውም፥ ልጅም ሆነ ወን​ድም የለ​ውም፤ ለድ​ካሙ ግን መጨ​ረሻ የለ​ውም፥ ዐይ​ኖ​ቹም ከባ​ለ​ጠ​ግ​ነት አይ​ጠ​ግ​ቡም። ለማን እደ​ክ​ማ​ለሁ? ሰው​ነ​ቴ​ንስ ከደ​ስታ ለምን እነ​ፍ​ጋ​ታ​ለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።


ብርን የሚ​ወ​ድድ ሰው ብርን አይ​ጠ​ግ​ብም፤ ብዙ እህ​ል​ንም የሚ​ወ​ድድ እን​ዲሁ ነው፤ ይህም ከንቱ ነው።


ከን​ቱን የሚ​ያ​በዛ ብዙ ነገር አለና፥ ለሰው ጥቅሙ ምን​ድር ነው?


ዓለም ባለ​ማ​ወቅ ለከ​ንቱ ነገር ተገ​ዝ​ቶ​አ​ልና በተ​ስፋ ስለ አስ​ገ​ዛው ነው እንጂ በፈ​ቃዱ አይ​ደ​ለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos