La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 144:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መን​ግ​ሥ​ትህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሁሉ መን​ግ​ሥት ናት፥ ግዛ​ት​ህም ለልጅ ልጅ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጐተራዎቻችን በተለያየ የእህል ዐይነት፣ የተሞሉ ይሁኑ፤ በጎቻችን እስከ ሺሕ ይውለዱ፤ በመስኮቻችንም እስከ ዐሥር ሺሕ ይባዙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዕቃ ቤቶቻቸንም ይሞሉ፥ በየዓይነቱም ዕቃ ይኑራቸው፥ በጎቻቸንም ብዙ ይውለዱ፥ በማሰማርያችንም ይብዙ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጐተራዎቻችን በልዩ ልዩ ዐይነት እህል የተሞሉ ይሁኑ፤ በመስኮቻችን ላይ የተሰማሩት በጎች በሺህ የሚቈጠሩ ግልገሎችን እየወለዱ ይብዙ።

Ver Capítulo



መዝሙር 144:13
10 Referencias Cruzadas  

ብዙ ጊዜ የተ​ቀ​መ​ጠ​ውን፥ የከ​ረ​መ​ው​ንም እህል ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ አዲ​ሱ​ንም ታስ​ገቡ ዘንድ የከ​ረ​መ​ውን ታወ​ጣ​ላ​ችሁ።


የእ​ህ​ሉም ማበ​ራ​የት በእ​ና​ንተ ዘንድ እስከ ወይኑ መቈ​ረጥ ይደ​ር​ሳል፤ የወ​ይ​ኑም መቈ​ረጥ እስከ እህሉ መዝ​ራት ይደ​ር​ሳል፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ግ​ቡም ድረስ እን​ጀ​ራ​ች​ሁን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በም​ድ​ራ​ች​ሁም ላይ ተዘ​ል​ላ​ችሁ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


የሆ​ድህ ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህም ፍሬ፥ የከ​ብ​ት​ህም ፍሬ፥ የላ​ም​ህም መንጋ፥ የበ​ግ​ህም መንጋ ቡሩክ ይሆ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ቱን በአ​ንተ ላይ፥ በጎ​ተ​ራህ፥ በእ​ህ​ል​ህም ሥራ ሁሉ እን​ዲ​ወ​ርድ ይል​ካል፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥ​ህም ምድር ይባ​ር​ክ​ሃል።


ሰውም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ በሚ​ወጣ ነገር ሁሉ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ኖር እንጂ ሰው በእ​ን​ጀራ ብቻ በሕ​ይ​ወት እን​ዳ​ይ​ኖር ያስ​ታ​ው​ቅህ ዘንድ አስ​ጨ​ነ​ቀህ፥ አስ​ራ​በ​ህም፤ አን​ተም ያላ​ወ​ቅ​ኸ​ውን፥ አባ​ቶ​ች​ህም ያላ​ወ​ቁ​ትን መና መገ​በህ።