እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፤ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።
እጅግ ተስፋ ቈርጫለሁና፣ ጩኸቴን ስማ፤ ከዐቅም በላይ ሆነውብኛልና፣ ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።
አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦ አንተ መጠጊያዬ ነህ፥ በሕያዋንም ምድር አንተ እድል ፈንታዬ ነህ አልሁ።
በጣም ተስፋ የቈረጥሁ ስለ ሆነ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጮኽ ስማኝ፤ እጅግ በርትተውብኛልና ከጠላቶቼ አድነኝ።
አቤቱ፥ ለእርሱ ትገለጥለት ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ታስበው ዘንድስ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
እጅህን ከአርያም ላክ፥ ከብዙ ውኃም አድነኝ፤ ከባዕድ ልጆችም እጅ፥
አቤቱ፥ በኀይሌ እወድድሃለሁ።
አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በእኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።
እግዚአብሔር ልዑል፥ ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና።
ለሕዝብህ ጭንቅን አሳየሃቸው፥ አስደንጋጩንም ወይን አጠጣኸን።
ከግብፅ የወይንን ግንድ አመጣህ፤ አሕዛብን አባረርህ፥ እርስዋንም ተከልህ።
በማለዳ ምሕረትህን፥ በሌሊትም እውነትህን መናገር፥
እንግዲህ እርሱ ራሱ ካጸደቀ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች የሚቃወማቸው ማነው?
ነገር ግን በወደደን በእርሱ ሁሉን ድል እንነሣለን።
የጥንት ምሳሌ፦ ‘ከኀጢአተኞች ኀጢአት ይወጣል’ እንደሚል፥ እጄ ግን በአንተ ላይ አትሆንም።