መዝሙር 128:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ያሳይህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ከጽዮን ይባርክህ፥ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢየሩሳሌምን መልካምነትዋን ታያለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ! የኢየሩሳሌምን ብልጽግና በሕይወትህ ዘመን ሁሉ እንድታይ ያድርግህ! |
ርስት ምድራቸውን ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፥ ለባሪያው ለእስራኤል ርስት አድርጎ የሰጠ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፥ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን” ይላሉ።
እነሆ፥ የመድኀኒታችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ዐይኖችህም ድንኳኖችዋ የማይናወጡ፥ ካስማዎችዋ ለዘለዓለም የማይነቀሉ፥ አውታሮችዋም ሁሉ የማይበጠሱ፥ የበለጸገች ከተማ ኢየሩሳሌምን ያያሉ።
በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።