በጭፍራውም ውስጥ ዳዊትን ለመርዳት የወጡ የተዘጋጁ፥ መሣሪያም ሁሉ የያዙ የዛብሎን ሰዎች አምሳ ሺህ ነበሩ፤ ከእነርሱ አንድስ እንኳ ደካማ አልነበረም።
መዝሙር 12:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ መቼ በነፍሴ ኀዘንን አኖራለሁ? እስከ መቼ ልቤ ሁልጊዜ ትጨነቅብኛለች? እስከ መቼ ጠላቶች በላዬ ይታበያሉ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዱ ለአንዱ ውሸትን ይናገራል፤ በሚያቈላምጥ አንደበት የሚናገሩትም በሁለት ልብ ነው። |
በጭፍራውም ውስጥ ዳዊትን ለመርዳት የወጡ የተዘጋጁ፥ መሣሪያም ሁሉ የያዙ የዛብሎን ሰዎች አምሳ ሺህ ነበሩ፤ ከእነርሱ አንድስ እንኳ ደካማ አልነበረም።
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ልመናዬንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም አድምጥ፥ ቸልም አትበለኝ፤ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶችም ሁሉ እንግዳ ነኝና።
በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፥ ጕሮሮኣቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
አንተም፦ የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማ፥ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እውነት ጠፍቶአል፤ ከአፋቸውም ተቈርጦአል ትላቸዋለህ።
ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ንግግራቸው ሽንገላ ነው፤ ለባልንጀራቸው ሰላምን ይናገራሉ፤ በልባቸው ግን ጥላቻን ይይዛሉ።
እነርሱ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያይደለ ለሆዳቸው ይገዛሉና፤ በነገር ማታለልና በማለዛዘብም የብዙዎች የዋሃንን ልብ ያስታሉ፤