ሕያው እንድሆን ቃልህንም እንድጠብቅ ለባሪያህ ስጠው።
ተርፌ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም፤ የእግዚአብሔርንም ሥራ ገና እናገራለሁ።
አልሞትም፥ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥ የጌታንም ሥራ እናገራለሁ።
በሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም፤ የእግዚአብሔርንም ድንቅ ሥራ ዐውጃለሁ።
ነፍሳቸው ትወጣለች፥ ወደ መሬትም ይመለሳሉ፤ ያንጊዜ ምክራቸው ሁሉ ይጠፋል።
አንተ ግን አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ እመልስላቸውም ዘንድ አስነሣኝ።
ጠላቶቼም በላዬ ክፋትን ይናገራሉ፦ “መቼ ይሞታል? ስሙስ መቼ ይሻራል?” ይላሉ።
በሞት የሚያስብህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?
እግዚአብሔር ፍርዳችንን አውጥቶአል፤ ኑ በጽዮን የአምላካችን የእግዚአብሔርን ሥራ እንናገር።
አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፣ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል።
ጌታችን ኢየሱስም ሰምቶ እንዲህ አለ፥ “ይህ ደዌ በእርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም።”