ትእዛዝህን አሰላሰልሁ፥ መንገድህንም እፈልጋለሁ።
በጻድቃን ድንኳን የእልልታና የሆታ ድምፅ፣ እንዲህ እያለ ያስተጋባል፤ “የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች፤
የእልልታና የመዳን ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይሉን አከናወነ።
በጻድቃን ድንኳን ውስጥ እንዲህ የሚል የድል አድራጊነት ድምፅ ይሰማል፦ “የእግዚአብሔር ኀይል ያሸንፋል!”
ዘሩ በምድር ላይ ኀያል ይሆናል፤ የጻድቃን ትውልዶች ይባረካሉ።
የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ የልቡም ዐሳብ ለልጅ ልጅ ነው።
ኀያል ሆይ፥ በደም ግባትህና በውበትህ፥ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ።
ፈሳሽ ወንዝ የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛል፤ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።
አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤ አቤቱ፥ እንደ አላባሽ ጋሻ ከለልኸን።
በጩኸት ደከምሁ፥ ጉሮሮዬም ሻከረ፤ አምላኬን ተስፋ ሳደርግ ዐይኖቼ ፈዘዙ።
አቤቱ፥ ተመለስ፥ እስከ መቼስ ነው? ስለ ባሪያዎችህም ተሟገት።
እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ደነገጡ፤ በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ፥ ምድርን አነዋወጣት።
አቤቱ፥ ቀኝህ በኀይል ከበረ፤ አቤቱ፥ ቀኝህ ጠላቶችን አደቀቀ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ባሪያዎች ይበላሉ፤ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ እነሆ፥ ባሪያዎች ይጠጣሉ፤ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ እነሆ፥ ባሪያዎች ደስ ይላቸዋል፤ እናንተ ግን ትጐሰቍላላችሁ፤
በክንዱ ኀይልን አደረገ፤ በልባቸው ዐሳብ የሚታበዩትንም በተናቸው።
ወደ ቤቱም አግብቶ ማዕድ አቀረበላቸው፤ በጌታችን ስለ አመነም እርሱ ከቤተ ሰቡ ጋር ደስ አለው።
እናንተም፥ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁም፥ ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለው በደጆቻችሁ ውስጥ የተቀመጠው ሌዋዊም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።
“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ! በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”