መዝሙር 114:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል ከግብጽ ወጥቶ ሲሄድ፣ የያዕቆብም ቤት ቋንቋው ልዩ ከሆነ ሕዝብ ተለይቶ ሲወጣ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሃሌ ሉያ! እስራኤል ከግብጽ፥ የያዕቆብም ቤት ከእንግዳ ሕዝብ በወጣ ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የያዕቆብ ዘሮች የሆኑት የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ በመውጣት የባዕድን አገር በለቀቁ ጊዜ |
ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁባትን ይህችን ቀን ዐስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በበረታች እጅ አውጥቶአችኋልና። ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
“በሚያዝያ ወር ከግብፅ ሀገር በሌሊት ወጥተሃልና የሚያዝያን ወር ጠብቀህ፥ የአምላክህ የእግዚአብሔርን ፋሲካ አድርግ።
እግዚአብሔርም በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ግርማ፥ በታላቅ ተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን፤