Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 114 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


እስራኤል ከግብጽ የወጡበት የፋሲካ መታሰቢያ መዝሙር

1 የያዕቆብ ዘሮች የሆኑት የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ በመውጣት የባዕድን አገር በለቀቁ ጊዜ

2 ይሁዳ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሆነ፤ እስራኤልም የእግዚአብሔር ርስት ሆነ።

3 ባሕር ይህን አይቶ ሸሸ፤ የዮርዳኖስም ወንዝ ውሃ ማፍሰሱን አቁሞ ወደ ኋላው ተመለሰ።

4 ተራራዎች እንደ አውራ በጎች ፈነጩ፤ ኰረብቶችም እንደ በግ ግልገል በየቦታው ዘለሉ።

5 አንተ ባሕር፥ ምን ሆነህ ሸሸህ? አንተስ ዮርዳኖስ፥ ስለምን መፍሰስህን አቁመህ ወደ ኋላህ ተመለስህ?

6 እናንተ ተራራዎች፥ ስለምን እንደ አውራ በጎች ፈነጫችሁ? እናንተስ ኰረብቶች፥ ስለምን እንደ በግ ግልገል በየቦታው ዘለላችሁ?

7 ምድር ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት፥ በያዕቆብም አምላክ ፊት በፍርሃት ተንቀጥቀጪ።

8 እርሱ አለቱን ወደ ኩሬ ውሃ፥ ጭንጫውንም ሸንተረር ወደ ወራጅ ምንጭ ይለውጣል።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos