Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 81:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አያ​ው​ቁም፥ አያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ምም፤ በጨ​ለማ ውስ​ጥም ይመ​ላ​ለ​ሳሉ፤ የም​ድር መሠ​ረ​ቶች ሁሉ ተና​ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሙሉ ለሙሉ ግብጽን ለቅቆ በወጣ ጊዜ፣ ይህን ለዮሴፍ ደነገገለት። በማላውቀውም ቋንቋ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ለእስራኤል ሥርዓቱ ነውና፥ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እርሱ ይህን ትእዛዝ ለዮሴፍ ልጆች የሰጣቸው ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ነው። ያልታወቀ ድምፅ እንዲህ ሲል እሰማለሁ፤

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 81:5
17 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የል​መ​ና​ዬን ድምፅ ሰም​ቶ​አ​ልና ወደ​ድ​ሁት።


ዓለ​ቱን በም​ድረ በዳ ሰነ​ጠቀ፤ ከብዙ ጥልቅ እን​ደ​ሚ​ገኝ ያህል አጠ​ጣ​ቸው።


በማ​ያ​ው​ቁ​ህም አሕ​ዛብ ላይ ስም​ህ​ንም በማ​ት​ጠራ መን​ግ​ሥት ላይ መዓ​ት​ህን አፍ​ስስ፤


ሙሴም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ኩለ ሌሊት እኔ በግ​ብፅ መካ​ከል እገ​ባ​ለሁ፤


እኔም በዚ​ያች ሌሊት በግ​ብፅ ሀገር አል​ፋ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም ሀገር ከሰው እስከ እን​ስሳ ድረስ በኵ​ርን ሁሉ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም አማ​ል​ክት ሁሉ ላይ በቀ​ልን አደ​ር​ግ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


‘ይህ በግ​ብፅ ሀገር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቤቶች ሰውሮ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶ​ቻ​ች​ንን የአ​ዳነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ሲ​ካው መሥ​ዋ​ዕት ነው’ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።” ሕዝ​ቡም ተጐ​ነ​በሱ፤ ሰገ​ዱም።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋን ከተ​ቀ​መ​ጠው ከፈ​ር​ዖን በኵር ጀምሮ እስከ ውኃ ቀጅዋ ምር​ኮኛ በኵር ድረስ፥ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ሩን ሁሉ፥ የእ​ን​ስ​ሳ​ው​ንም በኵር ሁሉ መታ።


በባ​ዕድ አፍ በል​ዩም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይና​ገ​ራል፤


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እነሆ ሕዝ​ብን ከሩቅ አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ኀያል ጥን​ታዊ ሕዝብ ነው፤ ቋን​ቋ​ቸ​ው​ንም የማ​ታ​ው​ቀው፥ የሚ​ና​ገ​ሩ​ት​ንም የማ​ታ​ስ​ተ​ው​ለው ሕዝብ ነው።


ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ቀድሱ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምል​ክት ይሁኑ።


በጽዋ የቀላ ወይን ለሚ​ጠጡ፥ እጅግ በአ​ማረ ሽቱም ለሚ​ቀቡ፥ በዮ​ሴፍ ስብ​ራት ለማ​ያ​ስቡ ወዮ​ላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንስር እን​ደ​ሚ​በ​ርር ከሩቅ ሀገር፥ ከም​ድር ዳር ቋን​ቋ​ቸ​ውን የማ​ት​ሰ​ማ​ውን ሕዝብ፥


ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የተ​ና​ገ​ረው ምስ​ክ​ርና ሥር​ዐት፤ ፍር​ድም ይህ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos