ከአለቆች ጋር ከሕዝቡም አለቆች ጋር ያኖረው ዘንድ
ልቡ የጸና ነው፤ አይፈራምም፤ በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።
በጠላቶቹ ላይ እስኪኮራ ድረስ ልቡ ጽኑ ነው፥ አይፈራምም።
በእግዚአብሔር ያለው እምነት እጅግ የጸና ስለ ሆነ ከቶ አይፈራም፤ በመጨረሻም የጠላቶቹን ውድቀት ያያል።
ትእዛዝህን ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርም።
አቤቱ፥ የጽድቅህን ፍርድ ስማር በቅን ልብ አመሰግንሃለሁ።
ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።
አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላካችን ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።
አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘለዓለም ልዑል ነህ፤
የእግዚአብሔር መርገም በክፉዎች ቤት ነው፥ በጻድቃን ቤት ግን በረከት አለ።
ሌላ ልዩ ትምህርት አታምጡ፤ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና።