አሳም፥ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም፤ አቤቱ፥ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና ርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህም” ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
መዝሙር 11:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ ታዲያ ነፍሴን፣ “እንደ ወፍ ወደ ተራራ ብረሪ” ለምን ትሏታላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር። በጌታ ታመንሁ፥ ነፍሴን፦ እንዴት እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ሽሺ ትሉአታላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከለላዬ ነው፤ እንዴት “እንደ ወፍ ወደ ተራራዎች ሽሽ” ትሉኛላችሁ። |
አሳም፥ “አቤቱ፥ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ማዳን አይሳንህም፤ አቤቱ፥ አምላካችን ሆይ፥ በአንተ ታምነናልና፥ በስምህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥተናልና ርዳን፤ አቤቱ፥ አምላካችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህም” ብሎ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
ኢትዮጵያውያንና የልብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች የነበሩአቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አልነበሩምን? በእግዚአብሔር ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጣቸው።
ሳኦልም ዳዊትን ጠበቀው፤ በነጋው እንዲገድሉት መልእክተኞቹን ወደ ዳዊት ቤት ላከ፤ ሚስቱም ሜልኮል፥ “በዚህች ሌሊት ነፍስህን ካላዳንህ ነገ ትገደላለህ” ብላ ነገረችው።
ዮናታንም ደግሞ፥ “ቶሎ ፍጠን፤ አትቈይ” ብሎ ወደ ብላቴናው ጮኸ፤ የዮናታንም ብላቴና ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው መጣ።
ዳዊትም ከዚያ በሞዓብ ምድር ወዳለችው ወደ መሴፋ ሄደ፤ የሞዓብንም ንጉሥ፥ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ አባቴና እናቴ ከአንተ ጋር ይቀመጡ ዘንድ እለምንሃለሁ” አለው።
ዳዊትም በምድረ በዳ በጠባቡ በማሴሬም ይኖር ነበር፥ በአውክሞዲስ ውስጥም በዚፍ ተራራ ምድረ በዳ ተቀመጠ፤ ሳኦልም ሁልጊዜ ይፈልገው ነበር፤ እግዚአብሔር ግን በእጁ አሳልፎ አልሰጠውም።
ዳዊትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳኦል እጅ እሞታለሁ፤ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ከመሸሸ በቀር የሚሻለኝ የለም፤ ሳኦልም በእስራኤል አውራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተዋል፤ እንዲሁም ከእጁ እድናለሁ” አለ።