ማርና ቅቤ፥ በግና ላም ይበሉ ዘንድ ለዳዊትና ከእርሱ ጋር ላሉ ሰዎች አመጡ። ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርበውና ተጠምተው ደክመው ነበርና።
መዝሙር 107:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥ ክብሩም በምድር ሁሉ ላይ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተራቡ፤ ተጠሙ፤ ነፍሳቸውም በውስጣቸው ዛለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተራቡ፥ ተጠሙም፥ ነፍሳቸውም ዛለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተርበውና ተጠምተው ስለ ነበር፥ ተስፋ ቈረጡ። |
ማርና ቅቤ፥ በግና ላም ይበሉ ዘንድ ለዳዊትና ከእርሱ ጋር ላሉ ሰዎች አመጡ። ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርበውና ተጠምተው ደክመው ነበርና።
የእስራኤልም ልጆች አሉአቸው፥ “በሥጋው ምንቸት አጠገብ ተቀምጠን እስክንጠግብ ድረስ እንጀራና ሥጋ በምንበላበት ጊዜ በግብፅ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን! ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልትገድሉ እኛን ወደዚች ምድረ በዳ አምጥታችኋልና።”
ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ “እኛንና ልጆቻችንን፥ ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብፅ አወጣኸን?” ሲሉ በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ።
ብረት ሠሪ መጥረቢያውን ይስላል፤ ጣዖቱን በመጥረቢያ ይቀርጸዋል፤ በመዶሻም መትቶ ቅርጽ ይሰጠዋል፤ በክንዱም ኀይል ይሠራዋል፤ እርሱም ይራባል፤ ይደክምማል፤ ውኃም አይጠጣም።
ወደ ሜዳ ብወጣ፥ እነሆ በሰይፍ የሞቱ አሉ፤ ወደ ከተማም ብገባ፥ እነሆ በራብ የከሱ አሉ፤ ነቢዩና ካህኑ ወደማያውቋት ሀገር ሄደዋልና።”
ቆፍ። ተነሺ፤ በሌሊት በመጀመሪያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፤ በጎዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።