Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 17:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሕዝ​ቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ “እኛ​ንና ልጆ​ቻ​ች​ንን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም በጥ​ማት ልት​ገ​ድል ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን?” ሲሉ በሙሴ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ነገር ግን ሕዝቡ በዚያ ተጠምተው ስለ ነበር፣ በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። እነርሱም፣ “እኛና ልጆቻችን እንዲሁም ከብቶቻችን በውሃ ጥም እንድናልቅ፣ ከግብጽ ለምን አወጣኸን?” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ ሕዝቡም በሙሴ ላይ አጉረመረሙ “እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብጽ አወጣኸን?” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሕዝቡ ግን እጅግ ተጠምተው ስለ ነበር “ከግብጽ ምድር ያወጣኸን ለምንድን ነው? እኛንና ልጆቻችንን እንስሶቻችንንም ጭምር በውሃ ጥም ለመፍጀት ነውን?” እያሉ በሙሴ ላይ ማጒረምረማቸውን ቀጠሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፦ እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብፅ አወጣኽን? ሲሉ በሙሴ ላይ አንጎራጎሩ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 17:3
9 Referencias Cruzadas  

ሕዝ​ቡም፥ “ምን እን​ጠ​ጣ​ለን?” ብለው በሙሴ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


ደግ​ሞም ሌላ ብዙ ድብ​ልቅ ሕዝብ፥ መን​ጎ​ችና ላሞ​ችም እጅግ ብዙም ከብ​ቶች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወጡ።


በግ​ብፅ ምድ​ርና በም​ድረ በዳ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴ​ንና ክብ​ሬን ያዩ እነ​ዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ስላ​ል​ሰሙ፥


እኛ፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ንም በዚያ እን​ሞት ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማኅ​በር ወደ​ዚህ ምድረ በዳ ለምን አወ​ጣ​ችሁ?


ሙሴ​ንም አሉት፥ “በግ​ብፅ መቃ​ብር ስላ​ል​ኖረ በም​ድረ በዳ እን​ሞት ዘንድ አወ​ጣ​ኸን? ከግ​ብፅ ታወ​ጣን ዘንድ ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው?


ለራ​ባ​ቸ​ውም ከሰ​ማይ እን​ጀ​ራን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ ለጥ​ማ​ታ​ቸ​ውም ከዓ​ለቱ ውኃን አወ​ጣ​ህ​ላ​ቸው፤ ትሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ እጅ​ህን የዘ​ረ​ጋ​ህ​ባ​ትን ምድር ገብ​ተው ይወ​ር​ሷት ዘንድ አዘ​ዝ​ሃ​ቸው።


ያስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ውም ዘንድ መል​ካ​ሙን መን​ፈ​ስ​ህን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ መና​ህ​ንም ከአ​ፋ​ቸው አል​ከ​ለ​ከ​ል​ህም፤ ለጥ​ማ​ታ​ቸ​ውም ውኃን ሰጠ​ሃ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ማ​ያት ላይ ከፍ ከፍ አለ፥ ክብ​ሩም በም​ድር ሁሉ ላይ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios