መዝሙር 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ጻድቁንና ኃጥኡን ይመረምራል፤ ዐመፃን የወደዳት ግን ነፍሱን ጠልቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገዱ ዘወትር የተሳካ ነው፤ ዕቡይ፣ ከሕግህም የራቀ ነው። በመሆኑም በጠላቶቹ ላይ ያፌዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገዱ ሁልጊዜ የጸና ነው፥ ፍርድህ ከእርሱ በላይ እጅግ ከፍ ያለ ነው፥ በጠላቶቹ ላይ ግን ይቀልዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰው በሁሉ ነገር ይሳካለታል፤ የእግዚአብሔርን ፍርድ ግን ሊረዳ አይችልም፤ በጠላቶቹም ላይ ይሳለቃል። |
ዳዊትና ሰዎቹም በሀገሩ ውስጥ ወደሚኖሩት ወደ ኢያቡሴዎናውያን ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፤ እነርሱም ዳዊትን፥ “ወደዚህ አትገባም” አሉት። ዕውሮችና አንካሶችም ወደዚህ አትገባም ብለው ተቃወሙት።
ሁለቱም የዐመፅ ልጆች የሆኑ ሰዎች ገብተው በፊቱ ቆሙ፤ “እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድበሃል” ብለው መሰከሩበት። የዚያ ጊዜም ከከተማ አውጥተው በድንጋይ ደብድበው ገደሉት።
አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
እናንተም “ከሲኦል ጋር ተማምለናል፤ ከሞትም ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፤ ሐሰትንም መሸሸጊያን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና፥ ዐውሎ ነፋስም ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም” ትላላችሁና፥
ስለዚህ የቍጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አመጣባቸው፤ በዙሪያቸው አቃጠላቸው፤ እነርሱ ግን አላወቁም፤ በልባቸውም አላስተዋሉም።
በመሰንቆና በበገና፥ በከበሮና በእምቢልታም እየዘፈኑ የወይን ጠጅን ይጠጣሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፤ የእጁንም ሥራ አላስተዋሉም።
ከእንግዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤፍሬም ምንድን ነው? እኔ አደከምሁት፤ አጸናሁትም፤ እኔ እንደ ተወደደ አበባ አፈራዋለሁ፤ ፍሬህም በእኔ ዘንድ ይገኛል።
ወደ እርሻውም ወጡ፤ ወይናቸውንም ለቀሙ፤ ጠመቁትም፤ የደስታም በዓል አደረጉ፤ ወደ አምላካቸውም ቤት ገቡ፤ በሉም፤ ጠጡም፤ አቤሜሌክንም ረገሙት።
ዜቡልም፥ “እንገዛለት ዘንድ አቤሜሌክ ማን ነው? ያልህበት አፍህ አሁን የት አለ? ይህ የናቅኸው ሕዝብ አይደለምን? አሁንም ወጥተህ ከእነርሱ ጋር ተዋጋ” አለው።