La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የኃጥኣን መንገዶች ግን ጨለማ ናቸው። እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ ምን እንደሚያሰናክላቸውም አያውቁም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የክፋት መንገድ እንደ ጨለማ ነው፥ እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ ይወድቃሉ፤ የመውደቂያቸው ምክንያት ምን እንደ ሆነ አያውቁም።

Ver Capítulo



ምሳሌ 4:19
16 Referencias Cruzadas  

ብር​ሃ​ንም ሳይ​ኖር በጨ​ለማ ይር​መ​ሰ​መ​ሳሉ፤ እንደ ሰካ​ራ​ምም ይፍ​ገ​መ​ገ​ማሉ።


ከብ​ር​ሃን ወደ ጨለማ አር​ቀው ያፈ​ል​ሱ​ታል።


በቀን ጨለማ ያገ​ኛ​ቸ​ዋል፥ በቀ​ት​ርም ጊዜ በሌ​ሊት እን​ዳሉ ይር​መ​ሰ​መ​ሳሉ።


በአ​ን​ድ​ነት ተካ​ክ​ለው ተማ​ክ​ረ​ዋ​ልና፤ በአ​ንተ ላይ ሤራ ቈረጡ፤ ቃል ኪዳ​ንም አደ​ረጉ፤


እነርሱ በጨለማ መንገድ ይሄዱ ዘንድ የቀናውን ጎዳና ለሚተዉ፥


እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ያመልጣል።


ሳይ​ጨ​ል​ም​ባ​ችሁ፥ ጨለ​ማም ባለ​ባ​ቸው ተራ​ሮች እግ​ሮ​ቻ​ችሁ ሳይ​ሰ​ነ​ካ​ከሉ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርን ስጡ፤ በዚ​ያም የሞት ጥላ አለና በጨ​ለ​ማ​ውም ውስጥ ያኖ​ራ​ች​ኋ​ልና ብር​ሃ​ንን ተስፋ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።


ስለ​ዚህ መን​ገ​ዳ​ቸው ድጥና ጨለማ ትሆ​ን​ባ​ቸ​ዋ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ፍግ​ም​ግም ብለው ይወ​ድ​ቁ​ባ​ታል፤ እኔም በም​ጐ​በ​ኛ​ቸው ዓመት ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ፤” አለ።


የዚያን ጊዜም ‘ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ አመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ’ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።


በሌ​ሊት የሚ​ሄድ ግን ይሰ​ነ​ካ​ከ​ላል፤ በው​ስጡ የሚ​ያ​የው ብር​ሃን የለ​ምና።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ ገና ለጥ​ቂት ጊዜ ብር​ሃን ከእ​ና​ንተ ጋር ነው፤ በጨ​ለማ የሚ​መ​ላ​ለስ የሚ​ሄ​ድ​በ​ትን አያ​ው​ቅ​ምና ጨለማ እን​ዳ​ያ​ገ​ኛ​ችሁ ብር​ሃን ሳለ​ላ​ችሁ ተመ​ላ​ለሱ፤


ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።


ለሚ​ጸ​ልይ ጸሎ​ቱን ይሰ​ጠ​ዋል፤ የጻ​ድ​ቃ​ንን ዘመን ይባ​ር​ካል፤ የሰው ኀይል ጽኑዕ አይ​ደ​ለ​ምና።