“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
ምሳሌ 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥ እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔርን መሪ አድርገው፤ እርሱም በትክክለኛው መንገድ ይመራሃል። |
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
ያባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በኢየሩሳሌም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት ያከብር ዘንድ ይህን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥
ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባሪያህን ጸሎት፥ ስምህንም ይፈሩ ዘንድ የሚወድዱትን የባሪያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬም ለባሪያህ አከናውንለት፤ በዚህም ሰው ፊት ምሕረትን ስጠው።” እኔም ለንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርሁ።
እግዚአብሔርም ታላላቆቹንና ሹሞቹን፥ ሕዝቡንም ሰብስቤ በየትውልዳቸው እቈጥራቸው ዘንድ ልቤን አነሣሣ፤ አስቀድመው የመጡትንም ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፤ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ።
እኔ ቂሮስን በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ፤ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ፤ እርሱ ከተማዬን ይሠራል፤ በዋጋም ወይም በጉቦ ሳይሆን ምርኮኞችን ያወጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”
ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እንዲህ ይላል፥ “እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ የምትሄድባትንም መንገድ እንዴት እንደምታገኝ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።
ደመናው ድንኳኑን በጋረደበት ቀን ቍጥር ሁሉ የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ቃል ይሰፍሩ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር።
በቃልም ቢሆን፥ ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አድርጉ፤ ስለ እርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑት።
ዳዊትም፥ “የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን? አገኛቸዋለሁን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እርሱም፥ “ታገኛቸዋለህና፥ ፈጽመህም ምርኮኞቹን ታድናለህና ፍለጋቸውን ተከተል” ብሎ መለሰለት።