ዘመኑ ለክፉዎች አይሆንምና የኃጥኣንም መብራት ይጠፋልና።
ግፈኛ ተስፋ የለውምና፤ የክፉዎችም መብራት ድርግም ብላ ትጠፋለች።
ለክፉ ሰው የወደፊት ተስፋ የለውምና፥ የክፉዎች መብራት ይጠፋልና።
ዐመፀኛ ሰው “ወደ ፊት ይህን አገኛለሁ” ብሎ ተስፋ የሚያደርገው ነገር የለውም።
ለመኖር ተስፋ አያደርግም፤ ፍጻሜው ከንቱ ይሆናልና።
የኃጥኣን መብራት ትጠፋለች፤ መቅሠፍትም ትመጣባቸዋለች። የበቀል ቍጣም ይይዛቸዋል፤
በምድር ላይ እንደ ተፈተነ፥ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር የእግዚአብሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው።
ፍላጾችህ ወግተውኛልና፥ እጅህንም በእኔ ላይ አክብደህብኛልና።
ኀጢአተኞች ወደ ሲኦል ይመለሱ፥ እግዚአብሔርን የሚረሱ አሕዛብም ሁሉ።
ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤ የኃጥኣን መብራት ግን ትጠፋለች። የሐሰተኞች ነፍሳት በኀጢአት ይስታሉ። ጻድቃን ግን ይራራሉ፥ ይመጸውታሉም።
ጠማማ ልብ ያለው መልካም ነገርን አያገኝም፥ አንደበቱን የሚለዋውጥም በክፉ ላይ ይወድቃል።
አባቱንና እናቱን የሚያማ ብርሃኑ ይጠፋል፥ የዐይኖቹ ብሌንም ጨለማን ያያል።
ለስድብ በልብ አለመቸኮል ታላቅ ዕውቀት ነው የኃጥኣንም ብርሃናቸው ኀጢአት ነው።
ብትጠብቃቸው ዘመድ ይሆኑሃል፥ ተስፋህም አትጠፋም።
እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደረግበታልና ለበደለኛ ወዮ! ክፉም ይደርስበታል።
ሰነፎቹም ልባሞቹን ‘መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን፤’ አሉአቸው።
የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”
የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።