በዚያችም ሌሊት አባታቸውን ወይን አጠጡት፤ ታላቂቱም ገባች፤ በዚያችም ሌሊት ከአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛም፥ ስትነሣም አላወቀም።
ምሳሌ 23:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ ዋይታ ለማን ነው? ጠብ ለማን ነው? ጩኸት ለማን ነው? ያለ ምክንያት መቍሰል ለማን ነው? የዐይን ቅላት ለማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዋይታ የማን ነው? ሐዘንስ የማን ነው? ጠብ የማን ነው? ብሶትስ የማን ነው? በከንቱ መቍሰል የማን ነው? የዐይን ቅላትስ የማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዋይታ ለማን ነው? ኀዘን ለማን ነው? ጠብ ለማን ነው? ጩኸት ለማን ነው? ያለ ምክንያት መቁሰል ለማን ነው? የዐይን ቅላት ለማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐዘንና ትካዜ የሚደርስበት ማን ነው? ዘወትር ክርክርና ጭቅጭቅ የሚያነሣሣ ማን ነው? ምክንያቱን ሳያውቅ ተፈንክቶ የሚገኝ ማን ነው? ዐይኑ የሚቀላበት ማን ነው? |
በዚያችም ሌሊት አባታቸውን ወይን አጠጡት፤ ታላቂቱም ገባች፤ በዚያችም ሌሊት ከአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛም፥ ስትነሣም አላወቀም።
ዳዊትም ጠራው፤ በፊቱም በላና ጠጣ፤ አሰከረውም፤ ነገር ግን በመሸ ጊዜ ወጥቶ ከጌታው አገልጋዮች ጋር በምንጣፉ ላይ ተኛ፤ ወደ ቤቱም አልወረደም።
አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ፤ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፥ “አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁ ጊዜ ግደሉት። አትፍሩም፤ ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘዛቸው።