ምሳሌ 21:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተወደደ መዝገብ በጠቢባን አፍ ያርፋል፤ አላዋቂዎች ግን ያጡታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጠቢብ ቤት ምርጥ ምግብና ዘይት ተከማችቶ ይገኛል፤ ሞኝ ሰው ግን ያለ የሌለውን ያሟጥጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፥ አእምሮ የሌለው ሰው ግን ያሟጥጠዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብልኅ ሰው ብዙ ሀብትና ውድ ነገሮችን በቤቱ ያከማቻል፤ ማስተዋል የጐደለው ሰው ግን ያለውን ሁሉ ያባክናል። |
ለሚወድዱኝ ሀብትን እከፍላቸው ዘንድ ቤተ መዛግብታቸውንም በመልካም ነገር እሞላ ዘንድ። የሚሆነውን ነገር በየቀኑ ብነግራችሁ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን ቍጥር አስባለሁ።
እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ ባለጠግነትንና ሀብትን መስጠቱ፥ ከእርስዋም ይበላና ዕድል ፈንታውን ይወስድ ዘንድ፥ በድካሙም ደስ ይለው ዘንድ ማሠልጠኑ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው።
በዚያም የተገኙ ዐሥር ሰዎች ቀርበው እስማኤልን እንዲህ አሉት፥ “በሜዳው ድልብ አለንና፥ ገብስና ስንዴ፥ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን፤” እርሱም በወንድሞቻቸው መካከል እነርሱን መግደል ተወ።
ጌታችን ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፥ “መጋቢ የነበረው አንድ ባለጸጋ ሰው ነበረ፤ ገንዘቡን ሁሉ እንደሚበትን አድርገው በእርሱ ዘንድ ከሰሱት።
መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካምን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከልቡ ክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል፤ ከልብ የተረፈውን አፍ ይናገራልና።