ምሳሌ 14:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰነፎች አፍ የስድብ በትር ይወጣል፤ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቂል ሰው ንግግር ለጀርባው በትር ታስከትልበታለች፤ የጥበበኛ ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰነፍ አፍ የትዕቢት በትር አለ፥ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኝን የገዛ ንግግሩ ያስቀጣዋል፤ ጥበበኞችን ግን መልካም አነጋገራቸው ይጠብቃቸዋል። |
አቤቱ አምላኬ፥ ተመልከተኝ ስማኝም፤ ለሞትም እንዳያንቀላፉ ዐይኖቼን አብራቸው። ጠላቶቼም አሸነፍነው እንዳይሉ፥
ሐሰትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የሥራውንም መቅሠፍት ይፈጽማል። እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚሰጥ ሰውን ይወድዳል፥ ከንቱ ሥራውን ግን ይጠላል።
አትመኩ፤ የኵራት ነገሮችንም አትናገሩ፤ ፅኑዕ ነገርም ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ዙፋኑን ያዘጋጃል።