ምሳሌ 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግ ሰው ከጽድቅ ፍሬ መልካምን ይበላል፤ የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በጨርቋነታቸው ይጠፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ከከንፈሩ ፍሬ መልካም ነገር ያገኛል፤ ወስላቶች ግን ዐመፅን ይናፍቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ይበላል፥ የዓመፀኞች ነፍስ ግን ግፍን ትሻለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች የመልካም አነጋገራቸውን ዋጋ ይቀበላሉ፤ የአታላዮች ምኞት ግን የግፍ ሥራ ለመፈጸም ነው። |
ዐመፅን ለምን ተከላችሁ? ኀጢአትንስ ለምን አጨዳችሁ፤ የሐሰትንም ፍሬ በልታችኋል፤ በሠረገሎችህና በሠራዊትህ ብዛት ታምነሃል።
የሰውንም ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ይከድንሃል፣ የአራዊትም አደጋ ያስፈራራሃል።
የሰውን ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ አንተ ብዙዎችን አሕዛብን በዝብዘሃልና ከአሕዛብ የቀሩት ሁሉ ይበዘብዙሃል።