Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 1:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ስለዚህ የሥራቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ በራሳቸውም ኀጢአት ይጠግባሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፤ የዕቅዳቸውንም ውጤት ይጠግባሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፥ የገዛ ራሳቸውን ምክር ይጠግባሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ስለዚህ የሚገባችሁን ቅጣት ትቀበላላችሁ፤ የተንኰላችሁንም ውጤት ታገኛላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 1:31
17 Referencias Cruzadas  

ልበ ትዕቢተኛ ከራሱ መንገድ ይጠግባል። ደግ ሰውም ከራሱ ዐሳብ ይጠግባል።


ምድር ሆይ፥ ስሚ! እነሆ ቃሌን ስላ​ል​ሰሙ፥ ሕጌ​ንም ስለ ጣሉ፥ እኔ​ንም ስለ ናቁ በዚህ ሕዝብ ላይ እንደ ሥራ​ቸው ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ሐሰትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ የሥራውንም መቅሠፍት ይፈጽማል። እግዚአብሔር ደስ ብሎት የሚሰጥ ሰውን ይወድዳል፥ ከንቱ ሥራውን ግን ይጠላል።


እኔ እን​ዳ​የሁ፥ ኀጢ​ኣ​ትን የሚ​ያ​ርሱ፥ የሚ​ዘ​ሩ​አ​ትም መከ​ራን ለራ​ሳ​ቸው ያጭ​ዳሉ።


ክፋ​ትሽ ይገ​ሥ​ጽ​ሻል፤ ክዳ​ት​ሽም ይዘ​ል​ፍ​ሻል፤ እኔን መተ​ው​ሽም ክፉና መራራ ነገር መሆ​ኑን ታው​ቂ​ያ​ለሽ፤ ትረ​ጂ​ማ​ለሽ” ይላል አም​ላ​ክሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “መፈ​ራ​ቴም በአ​ንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላ​ሰ​ኘ​ኝም” ይላል አም​ላ​ክሽ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ኀጢአት ሰውን ያጠምዳል፥ ሁሉም በኀጢአቱ ልባብ ይታሰራል።


እርሱ ከሰነፎች ጋር ይሞታል፤ ከስንፍናውም ብዛት የተነሣ ሕይወቱ ይጣላል፤ ስለ ስንፍናውም ይጠፋል።


በእኔ ላይ በደልን የሚፈጽሙ ራሳቸውን ይበድላሉ፤ የሚጠሉኝም ሞትን ይወድዳሉ።


የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥ ሰውም የከንፈሩን ዋጋ ይቀበላል።


ደግ ሰው ከጽድቅ ፍሬ መልካምን ይበላል፤ የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በጨርቋነታቸው ይጠፋሉ።


እኔ ግን አዋ​ር​ዳ​ቸው ዘንድ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም እበ​ቀ​ላ​ቸው ዘንድ እፈ​ቅ​ዳ​ለሁ፤ እኔ በጠ​ራሁ ጊዜ አል​መ​ለ​ሱ​ል​ኝ​ምና፥ በተ​ና​ገ​ር​ሁም ጊዜ አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ በፊ​ቴም ክፉ ነገ​ርን አደ​ረጉ፤ ያል​ወ​ደ​ድ​ሁ​ት​ንም መረጡ።”


ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ሩ​ላ​ቸ​ውም ሰዎች ከራ​ብና ከሰ​ይፍ የተ​ነሣ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች ይበ​ተ​ናሉ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ው​ንም አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና እነ​ር​ሱ​ንና ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም የሚ​ቀ​ብ​ራ​ቸው አይ​ገ​ኝም።


እንደ ሥራ​ች​ሁም ፍሬ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዱ​ር​ዋም ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ይበ​ላል።”


ስለ​ዚህ ቍጣ​ዬን አፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤ በመ​ዓ​ቴም እሳት አጠ​ፋ​ኋ​ቸው፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንም በራ​ሳ​ቸው ላይ መለ​ስሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios