ምሳሌ 12:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥ ሰውም የከንፈሩን ዋጋ ይቀበላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ከከንፈሩ ፍሬ የተነሣ በበጎ ነገር ይሞላል፤ እንደ እጁ ሥራም ተገቢውን ዋጋ ያገኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥ ሰውም እንደ እጁ ሥራ ዋጋውን ይቀበላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምታገኘው በረከት የመልካም ንግግርህና ሥራህ ውጤት ነው፤ በዚህ ዐይነት ተገቢ ዋጋህን ታገኛለህ። |
እነሆ፥ ይህን አላውቅም ብትል፥ እግዚአብሔር የሁሉን ልብ እንዲያውቅ ዕወቅ። ለሁሉ እስትንፋስን የፈጠረ እርሱ ሁሉን ያውቃል። ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፍለዋል።
እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ፤ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።”
እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።”
የክርስቶስ የመስቀሉ ተግዳሮት ከግብፅ ሀብት ሁሉ ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ባለጠግነት እንደሚሆን ዐውቆአልና፥ ዋጋውንም ተመልክቶአልና።