ምሳሌ 11:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጻድቃን ምኞት መልካም ነው፤ የኃጥኣን ተስፋ ግን ይጠፋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቃን ምኞት ምን ጊዜም ፍጻሜው ያማረ ነው፤ የክፉዎች ተስፋ ግን በቍጣ ያከትማል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቃን ምኞት በጎ ብቻ ነው፥ የክፉዎች ተስፋ ግን መቅሠፍት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደጋግ ሰዎች ምኞት ጥሩ ውጤት አለው፤ የክፉ ሰዎች ምኞት ግን ጥፋትን ያስከትላል። |
አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ትእዛዝህ በምድር ላይ ብርሃን ነውና ነፍሴ በሌሊት ወደ አንተ ትገሠግሣለች። በምድር የምትኖሩም ጽድቅ መሥራትን ተማሩ።
እኔም አንተን ተከትዬ አልደከምሁም፥ የሰውንም ቀን አልተመኘሁም፤ አንተ ታውቃለህ፤ ከከንፈሬ የወጣውም በፊትህ ነው።