ኮሎዶጎሞርንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ወግቶ ከተመለሰም በኋላ የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሜዳ በሆነ በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ።
ዘኍል 31:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም፥ የማኅበሩም አለቆች ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ሊገናኙአቸው ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ፣ ካህኑ አልዓዛርና የማኅበረ ሰቡ መሪዎች በሙሉ ሊቀበሏቸው ከሰፈር ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም የማኅበሩም አለቆች ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ሊገናኙአቸው ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ፥ አልዓዛርና ሌሎቹም የማኅበሩ መሪዎች ሠራዊቱን ለመቀበል ከሰፈር ወጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም የማኅበሩም አለቆች ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ሊገናኙአቸው ወጡ። |
ኮሎዶጎሞርንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ነገሥታት ወግቶ ከተመለሰም በኋላ የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሜዳ በሆነ በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ።
“መኰንንም ኀጢአትን ቢሠራ፥ ሳያውቅም እግዚአብሔር አምላኩ፦ አትሥራ ያለውን ትእዛዝ ቢተላለፍ፥ እንዲህም ቢበድል፥
የማረኩትን ምርኮውንና የዘረፉትን ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ እስራኤልም ልጆች፥ በዮርዳኖስም አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ወዳለው ሰፈር አመጡ።
“የእስራኤል ልጆች ለምጻሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገርም ያለበትን ሁሉ በሰውነቱ የረከሰውን ሁሉ ከሰፈሩ እንዲያወጡ እዘዛቸው፤
ሳሙኤልም እስራኤልን ለመገናኘት በጥዋት ገሥግሦ ሄደ። ለሳሙኤልም፥ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ መጣ፤ እነሆም፥ ለራሱ የመታሰቢያ ዐምድ አቆመ” ብለው ነገሩት። ሳሙኤልም ሰረገላውን መልሶ ወደ ጌልጌላ ወደ ሳኦል ወረደ፤ ከአማሌቅ ዘንድ ከአመጣውም ከአማረው ከምርኮው መንጋ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ሲሠዋ አገኘው፤
ዳዊትም ደክመው ዳዊትን ይከተሉት ዘንድ ወዳልቻሉ፥ በቦሦር ወንዝ ወዳስቀራቸው ወደ ሁለቱ መቶ ሰዎች መጣ፤ እነርሱም ዳዊትን ከእርሱም ጋር የነበሩትን ሕዝብ ሊቀበሉ ወጡ፤ ዳዊትም ወደ ሕዝቡ በቀረበ ጊዜ ደኅንነቱን ጠየቁት።