ደግሞም በእግዚአብሔር ስም አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ፤ ልቡንም አጠነከረ።
ዘኍል 30:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴትም ደግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል፥ እርስዋም በአባቷ ቤት ሳለች በብላቴንነቷ ጊዜ ራስዋን ብትለይ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በአባቷ ቤት የምትኖር ሴት ልጅ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል ወይም አንድ ነገር ለማድረግ በመሐላ ራሷን ግዴታ ውስጥ ብታስገባ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴትም ደግሞ በአባትዋ ቤት ሳለች በብላቴንነትዋ ጊዜ ለጌታ ስእለት ብትሳል፥ ወይም ራስዋን በመሐላ ብታስር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገና በአባትዋ ቤት የምትኖር ልጃገረድ ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ለመስጠት ብትሳል፥ ወይም ከአንድ ነገር ራስዋን ለመከልከል ቃል ብትገባ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴትም ደግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል፥ እርስዋም በአባትዋ ቤት ሳለች በብላቴንነትዋ ጊዜ ራስዋን በመሐላ ብታስር፥ |
ደግሞም በእግዚአብሔር ስም አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ፤ ልቡንም አጠነከረ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል አንተ እንደምትገምተው መጠን ስለ ሰውነቱ ዋጋውን ይስጥ።
ሰው ሁሉ ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል፥ ወይም መሐላን ቢምል፤ ራሱንም ቢለይ፥ ቃሉን አያርክስ፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ።
አባቷም ስእለቷንና ራስዋን የለየችበትን ቢሰማ፥ አባቷም ዝም ቢላት፥ ስእለቷ ሁሉ ይጸናል፤ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ ልዩ ስእለት ቢሳል፥
የማኅበሩም አለቆች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስለ ማሉላቸው የእስራኤል ልጆች አልገደሉአቸውም። ማኅበሩም ሁሉ በአለቆቹ ላይ አጕረመረሙ።
እርስዋንም ባየ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ፥ “ወዮልኝ ልጄ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር አፌን ከፍቻለሁና፥ ከዚያውም እመለስ ዘንድ አልችልምና አሰናከልሽኝ፤ አስጨነቅሽኝም” አላት።
እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።