Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 30:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሴትም ደግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል፥ እርስዋም በአባትዋ ቤት ሳለች በብላቴንነትዋ ጊዜ ራስዋን በመሐላ ብታስር፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 “በአባቷ ቤት የምትኖር ሴት ልጅ ለእግዚአብሔር ስእለት ብትሳል ወይም አንድ ነገር ለማድረግ በመሐላ ራሷን ግዴታ ውስጥ ብታስገባ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሴትም ደግሞ በአባትዋ ቤት ሳለች በብላቴንነትዋ ጊዜ ለጌታ ስእለት ብትሳል፥ ወይም ራስዋን በመሐላ ብታስር፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ገና በአባትዋ ቤት የምትኖር ልጃገረድ ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ለመስጠት ብትሳል፥ ወይም ከአንድ ነገር ራስዋን ለመከልከል ቃል ብትገባ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሴትም ደግሞ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ብት​ሳል፥ እር​ስ​ዋም በአ​ባቷ ቤት ሳለች በብ​ላ​ቴ​ን​ነቷ ጊዜ ራስ​ዋን ብት​ለይ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 30:3
10 Referencias Cruzadas  

ደግሞም በእግዚአብሔር አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ ልቡንም አጠነከረ።


ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሰውን ለእግዚአብሔር ሊሰጥ ቢሳል አንተ እንደምትገምተው መጠን ስለ ሰው ዋጋውን ይስጥ።


ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል፥ ወይም ራሱን በመሐላ ቢያስር፥ ቃሉን አይስበር፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ።


አባትዋም ራስዋን ያሰረችበትን መሐላ ስእለትዋንም ቢሰማ፥ አባትዋም ዝም ቢላት፥ ስእለትዋ ሁሉ ይጸናል፥ ራስዋንም ያሰረችበት መሐላ ሁሉ ይጸናል።


ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፦ ሰው ወይም ሴት ለእግዚአብሔር ራሱን የተለየ ያደርግ ዘንድ የናዝራዊነት ስእለት ቢሳል፥


ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ፤ ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና።


የሕዝቡም አለቆች በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስለ ማሉላቸው የእስራኤል ልጆች አልመቱአቸውም። ማኅበሩም ሁሉ በአለቆቹ ላይ አጉረመረሙ።


እርስዋንም ባየ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ፦ አወይ ልጄ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር አፌን ከፍቻለሁና፥ ከዚያውም እመለስ ዘንድ አልችልምና በጣም አዋረድሽኝ አስጨነቅሽኝም አላት።


እርስዋም፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ የባሪያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ እኔንም ባትረሳ፥ ለባሪያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ፥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፥ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም ብላ ስእለት ተሳለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos