Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 30:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሰው ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስእ​ለት ቢሳል፥ ወይም መሐ​ላን ቢምል፤ ራሱ​ንም ቢለይ፥ ቃሉን አያ​ር​ክስ፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድ​ርግ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት በሚሳልበት ወይም አንድ ነገር ለማድረግ በመሐላ ራሱን ግዴታ ውስጥ በሚያስገባበት ጊዜ ቃሉን ሳያጥፍ ያለውን ሁሉ መፈጸም አለበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሰው ለጌታ ስእለት ቢሳል፥ ወይም ራሱን በመሐላ ቢያስር፥ ቃሉን አያፍርስ፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አንድ ሰው ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ለመስጠት ቢሳል ወይም ከአንድ ነገር ራሱን ለመከልከል በመሐላ ቃል ቢገባ፥ አደርጋለሁ ያለውን ሁሉ መፈጸም አለበት እንጂ የሰጠውን የተስፋ ቃል ማስቀረት አይገባውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሰው ለእግዚአብሔር ስእለት ቢሳል፥ ወይም ራሱን በመሐላ ቢያስር፥ ቃሉን አይስበር፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 30:2
36 Referencias Cruzadas  

ወደ እር​ሱም ትጸ​ል​ያ​ለህ፥ እር​ሱም ይሰ​ማ​ሃል፤ ስእ​ለ​ት​ህ​ንም ይሰ​ጠ​ሃል።


ፈቃ​ድህ ሁሉ በም​ድር ባሉት ቅዱ​ሳን ላይ ተገ​ለጠ።


የመ​ድ​ኀ​ኒቴ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ከደም አድ​ነኝ፥ አን​ደ​በ​ቴም በአ​ንተ ጽድቅ ደስ ይለ​ዋል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ አስ​ታ​ወ​ስሁ፤ የቀ​ደ​መ​ውን ተአ​ም​ራ​ት​ህን አስ​ታ​ው​ሳ​ለ​ሁና፤


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በከ​ንቱ አት​ጥራ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።


ሰው ከገንዘቡ በችኮላ የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል፥ ከተሳለም በኋላ ቢፀፀት ወጥመድ ይሆንበታል።


ሰው ሳያ​ስብ ክፉን ወይም መል​ካ​ምን ያደ​ርግ ዘንድ ሳያ​ስብ በከ​ን​ፈሩ ተና​ግሮ ቢምል፥ ሳያ​ስብ የማ​ለ​ውም ከዚህ ባንዱ ነገር ቢሆን፥ በታ​ወ​ቀው ጊዜ ከዚህ ነገር በአ​ንዱ በደ​ለኛ ይሆ​ናል።


እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል።


እስ​ራ​ኤ​ልም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ይህን ሕዝብ አሳ​ል​ፈህ በእ​ጃ​ችን ብት​ሰ​ጠን እር​ሱ​ንና ከተ​ሞ​ቹን ሕርም ብለን እና​ጠ​ፋ​ዋ​ለን” ብለው ስእ​ለት ተሳሉ።


ሴትም በባ​ልዋ ቤት ሳለች ብት​ሳል፥ ወይም ራስ​ዋን በመ​ሐላ ብታ​ስር፥


ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ከተ​ሞ​ችን፥ ለበ​ጎ​ቻ​ች​ሁም በረ​ቶ​ችን ሥሩ፤ ከአ​ፋ​ች​ሁም የወ​ጣ​ውን ነገር አድ​ርጉ።”


“እናንተ ‘ማንም በቤተ መቅደስ የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በቤተ መቅደስ ወርቅ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል፤’ የምትሉ፥ ዕውሮች መሪዎች፥ ወዮላችሁ።


ደግማችሁም ‘ማንም በመሠዊያው የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በላዩ ባለው መባ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል፤’ ትላላችሁ።


በነ​ጋም ጊዜ አይ​ሁድ ተሰ​ብ​ስ​በው፥ ጳው​ሎ​ስን እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉት ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ ተስ​ማ​ም​ተው ተማ​ማሉ።


እነ​ር​ሱም ወደ ሊቃነ ካህ​ና​ትና ወደ መም​ህ​ራን ሄደው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ጳው​ሎ​ስን እስ​ክ​ን​ገ​ድ​ለው ድረስ እነሆ፥ እን​ዳ​ን​በ​ላና እን​ዳ​ን​ጠጣ ፈጽ​መን ተማ​ም​ለ​ናል።


አንተ ግን እሽ አት​በ​ላ​ቸው፤ ሊገ​ድ​ሉት ሽም​ቀ​ዋ​ልና፤ እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉ​ትም ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ እን​ዲህ የተ​ማ​ማሉ ሰዎች ከአ​ርባ ይበ​ዛሉ፤ አሁ​ንም እስ​ክ​ት​ል​ክ​ላ​ቸው ይጠ​ብ​ቃሉ እንጂ እነ​ርሱ ቈር​ጠ​ዋል።”


እኔ ለእ​ና​ንተ በመ​ራ​ራት ወደ ቆሮ​ን​ቶስ እን​ዳ​ል​መ​ጣሁ፥ ስለ ራሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ክር አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


ዮፍ​ታ​ሔም ከገ​ለ​ዓድ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጋር ሄደ፤ ሕዝ​ቡም መስ​ፍን ይሆ​ና​ቸው ዘንድ በላ​ያ​ቸው አለቃ አድ​ር​ገው ሾሙት፤ ዮፍ​ታ​ሔም ቃሉን ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ሴፋ ተና​ገረ።


ሁለት ወርም ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ ወደ አባቷ ተመ​ለ​ሰች፤ ዮፍ​ታ​ሔም የተ​ሳ​ለ​ውን ስእ​ለት አደ​ረገ፤ እር​ስ​ዋም ወንድ አላ​ወ​ቀ​ችም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos