ኢዮርብዓምም በስምንተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ አምስተኛው ቀን በይሁዳ እንደሚደረግ በዓል ያለ በዓል አደረገ፤ ለሠራቸውም ጥጆች ይሠዋ ዘንድ በቤቴል ወደ ሠራው መሠዊያ ወጣ፤ ለኮረብታ መስገጃዎችም የመረጣቸውን እነዚያን ካህናት በቤቴል አኖራቸው።
ዘኍል 29:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በሰባተኛውም ወር ዐሥራ አምስተኛዋ ቀን ለእናንተ የተቀደሰች ትሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩባት፤ ሰባት ቀንም ለእግዚአብሔር በዓል አድርጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በሰባተኛው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ሥራ አትሥሩ፤ ለእግዚአብሔርም የሰባት ቀን በዓል አክብሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰባተኛውም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፥ ሰባት ቀንም ለጌታ በዓል አድርጋችሁ ታከብራላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን በአንድነት ለማምለክ ትሰበሰባላችሁ፤ ይህንንም በዓል ለእግዚአብሔር ክብር በመስጠት ሰባት ቀን አክብሩ፤ በዚህም ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰባተኛውም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፥ ሰባት ቀንም ለእግዚአብሔር በዓል አድርጉ። |
ኢዮርብዓምም በስምንተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ አምስተኛው ቀን በይሁዳ እንደሚደረግ በዓል ያለ በዓል አደረገ፤ ለሠራቸውም ጥጆች ይሠዋ ዘንድ በቤቴል ወደ ሠራው መሠዊያ ወጣ፤ ለኮረብታ መስገጃዎችም የመረጣቸውን እነዚያን ካህናት በቤቴል አኖራቸው።
እንደ ተጻፈውም የዳስ በዓል አደረጉ፤ እንደ ሥርዐቱም ለየዕለቱ የተገባውን የየዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በቍጥር አቀረቡ።
በሰባተኛውም ወር ባለው በዓል የእስራኤል ልጆች በዳስ ይቀመጡ ዘንድ በከተሞቻቸውና በኢየሩሳሌምም ይናገሩና ያውጁ ዘንድ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ በሕጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ።
ከመጀመሪያውም ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉንም ሰባት ቀን ያህል አደረጉ፤ በስምንተኛውም ቀን እንደ ሕጋቸው ወጡ።
በፊቴ ባዶ እጅህን አትታይ። በእርሻም የምትዘራትን የፍሬህን በኵራት የመከር በዓል፥ ዓመቱም ሲያልቅ ፍሬህን ከእርሻ ባከማቸህ ጊዜ የመክተቻውን በዓል ጠብቅ።
የሰባቱንም ሱባዔ በዓል ታደርጋለህ፤ እርሱም የስንዴ መከር መጀመሪያ ነው፤ በዓመቱም መካከል የመክተቻ በዓል ታደርጋለህ።
በሰባተኛውም ወር ከወሩም በዐሥራ አምስተኛው ቀን በበዓሉ ሰባት ቀኖች፥ የኃጢአቱን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት፥ የእህሉንም ቍርባን ከዘይቱ ጋር እንዲሁ ያቅርብ።”
“በሰባተኛውም ወር ከወሩ የመጀመሪያዋ ቀን ለእናንተ ይህች ዕለት የተቀደሰች ናት፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩባት፤ ምልክት ያለባት ቀን ትሁንላችሁ።
ለእግዚአብሔርም በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ዐሥራ ሦስት በሬዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ ዐሥራ አራት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ፤ ነውር የሌለባቸውም ይሁኑ።