ዘኍል 28:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔርም ስለኀጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቍርባን ሌላ ይቀርባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመጠጥ ቍርባኑ ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት ሆኖ ለእግዚአብሔር ይቀርባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታም ለኃጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ፤ ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቁርባን ጎን ለጎን የሚቀርብ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየቀኑ ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ጋር የመጠጥ መባ በመጨመር አንድ ተባዕት ፍየል ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔርም ለኃጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቍርባን ሌላ ይቀርባል። |
“ስለ ሕዝቡም ኀጢአት የሚሠዋውን መሥዋዕት ፍየል ያርዳል፤ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ያመጣዋል፤ በወይፈኑም ደም እንዳደረገ በፍየሉ ደም ያደርጋል፤ በመክደኛው ላይና በመክደኛው ፊት ይረጨዋል።
ከእስራኤል ልጆች ርኩስነት፥ ከመተላለፋቸውም፥ ከኀጢአታቸውም የተነሣ ለመቅደሱ ያስተሰርይለታል፤ እንዲሁም በርኩስነታቸው መካከል ከእነርሱ ጋር ለኖረች ለምስክሩ ድንኳን ያደርጋል።
በማኅበሩም ፊት ያልታወቀ ኀጢአት ቢኖር፥ ማኅበሩ ሁሉ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ከመንጋዎች አንድ ንጹሕ ወይፈን ያቀርባሉ። የእህሉ ቍርባንና የመጠጡ ቍርባንም እንደ ሕጉ ነው፤ ለኀጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ያቀርባሉ።
የመጠጥ ቍርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሲሦ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።
እንዲህም በላቸው፦ በእሳት ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት ቍርባን ይህ ነው፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ።
ለኀጢአትም መሥዋዕት ከፍየሎች አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ የሚቀርቡ ናቸው።
ስለ ሥጋ ደካማነት የኦሪት ሕግ ከሞት ማዳን በተሳነው ጊዜ እግዚአብሔር በኀጢኣተና ሥጋ ምሳሌ ልጁን ላከ፤ ያችንም ኀጢአት በሥጋው ቀጣት።