Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 16:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርኩ​ስ​ነት፥ ከመ​ተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውም፥ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ለመ​ቅ​ደሱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ እን​ዲ​ሁም በር​ኩ​ስ​ነ​ታ​ቸው መካ​ከል ከእ​ነ​ርሱ ጋር ለኖ​ረች ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ያደ​ር​ጋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከእስራኤላውያን ርኩሰትና ዐመፅ፣ ከየትኛውም ኀጢአታቸው ይነጻ ዘንድ በዚህ ሁኔታ ለቅድስተ ቅዱሳኑ ያስተሰርይለታል፤ በርኩሰታቸው መካከል በእነርሱ ዘንድ ላለችውም የመገናኛዋ ድንኳን እንደዚሁ ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከእስራኤል ልጆች ርኩስነት፥ ከመተላለፋቸውም፥ ከኃጢአታቸውም ሁሉ የተነሣ ለተቀደሰው ስፍራ ያስተሰርይለታል፤ በርኩስነታቸውም መካከል ከእነርሱ ጋር ላለው ለመገናኛው ድንኳን እንዲሁ ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በዚህም ዐይነት ቅድስተ ቅዱሳኑን ከእስራኤል ሕዝብ ርኲሰትና ከኃጢአታቸውም ሁሉ ለማጥራት የማንጻትን ሥርዓት ይፈጽማል፤ ንጹሕ ባልሆነ ሰፈር መካከል ስለሚገኝ ድንኳኑንም ለማንጻት እንዲሁ ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከእስራኤል ልጆች ርኩስነት ከመተላለፋቸውም ከኃጢአታቸውም የተነሣ ለመቅደሱ ያስተሰርይለታል፤ እንዲሁም በርኩስነታቸው መካከል ከእነርሱ ጋር ለኖረች ለመገናኛው ድንኳን ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 16:16
12 Referencias Cruzadas  

በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ወዳ​ለው ወደ መሠ​ዊ​ያው ወጥቶ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ከወ​ይ​ፈ​ኑም ደም፥ ከፍ​የ​ሉም ደም ወስዶ በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ያሉ​ትን ቀን​ዶች ያስ​ነ​ካል።


አረ​ዱ​ትም፤ ሙሴም ደሙን ወስዶ በጣቱ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀን​ዶች ዙሪያ ቀባ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም አነ​ጻው፤ ደሙ​ንም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች አፈ​ሰ​ሰው፤ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ትም ዘንድ ቀደ​ሰው።


ከሄ​ድ​ሁና ቦታ ካዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ች​ሁም ዳግ​መኛ እመ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተም እኔ በአ​ለ​ሁ​በት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም የሕ​ዝ​ብን ኀጢ​አት ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ የሚ​ም​ርና የታ​መነ ሊቀ ካህ​ናት እን​ዲ​ሆን በነ​ገር ሁሉ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሊመ​ስል ተገ​ባው።


አሮ​ንም በዓ​መት አንድ ጊዜ በቀ​ን​ዶቹ ላይ ማስ​ተ​ስ​ረያ ያደ​ር​ጋል፤ በዓ​መት አንድ ጊዜ ኀጢ​አ​ትን ከሚ​ያ​ነ​ጻው ደም ይወ​ስ​ዳል፤ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ነጻ ያደ​ር​ጋል፤ ይህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።”


እርሱ ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ወደ መቅ​ደሱ በገባ ጊዜ ለራሱ፥ ለቤ​ተ​ሰ​ቡም፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ አስ​ተ​ስ​ርዮ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ማንም አይ​ኖ​ርም።


“በዚህ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ዐሥ​ረ​ኛዋ ቀን የማ​ስ​ተ​ስ​ረያ ቀን ናት፤ ቅድ​ስት ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አስ​ጨ​ን​ቋት፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አቅ​ርቡ።


ሙሴና አሮ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ​ኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከመ​ጠጡ ቍር​ባን ሌላ ይቀ​ር​ባል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios