ዘኍል 26:57 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሌዊ ልጆች በየወገናቸው የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው፤ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ወገን፥ ከቀዓት የቀዓታውያን ወገን፥ ከሜራሪ የሜራራውያን ወገን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየጐሣቸው የተቈጠሩት ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤ በጌርሶን በኩል፣ የጌርሶናውያን ጐሣ፣ በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጐሣ፣ በሜራሪ በኩል፣ የሜራራውያን ጐሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሌዋውያንም በየወገናቸው የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው፤ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ወገን፥ ከቀዓት የቀዓታውያን ወገን፥ ከሜራሪ የሜራራውያን ወገን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሌዋውያን ነገድ ተወላጆች፦ ጌርሾን፥ ቀዓት፥ ሜራሪና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። የእነርሱም ዘሮች ሊብኒ፥ ኬብሮን፥ ማሕሊ፥ ሙሴ፥ ቆሬና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው። ቀዓትም አሞራምን ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሌዋውያንም በየወገናቸው የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው፤ ከጌድሶን የጌድሶናውያን ወገን፥ ከቀዓት የቀዓታውያን ወገን፥ ከሜራሪ የሜራራውያን ወገን። |
የአሮንም ልጅ አልዓዛር ከፋትኤል ልጆች ሚስትን አገባ፤ እርስዋም ፊንሐስን ወለደችለት። እነዚህም በየወገኖቻቸው የሌዋውያን አባቶች አለቆች ናቸው።
“የሌዊን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በየወገናቸውም ቍጠር፤ ወንዱን ሁሉ ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን ቍጠራቸው።”