ዘኍል 23:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ አንበሳ ደቦል ያገሣል፤ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አይተኛም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይነሣል፤ ያደነውን እስኪያነክት፣ የገደለውንም ደም እስኪጠጣ፣ እንደማያርፍ አንበሳ ሆኖ ይነሣል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ብድግ ይላል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አያርፍም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ እንደ እንስት አንበሳ ይቆማል፤ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን ሳይበላና ደሙን ሳይጠጣ አያርፍም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይቆማል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አይተኛም። |
ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከመሰማሪያህ ወጣህ፤ እንደ አንበሳ ተኛህ፤ አንቀላፋህም፤ እንደ አንበሳም ደቦል የሚቀሰቅስህ የለም።
በስድስቱም እርከኖች ላይ በዚህና በዚያ ዐሥራ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር፤ በመንግሥታት ሁሉ እንዲህ ያለ ሥራ አልተሠራም።
ወደ ዙፋኑም የሚያስሄዱ፥ በወርቅ የተለበጡ ስድስት እርከኖች ነበሩ፤ በዚህና በዚያ በመቀመጫው አጠገብ ሁለት የክንድ መደገፊያዎች ነበሩበት፤ በመደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር።
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛልና፥ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ እንደሚያገሣ፥ ድምፁም ተራሮችን እስኪሞላ በእርሱ ላይ እንደሚጮህ፥ እረኞችም ሁሉ ሲጮሁበት ከብዛታቸው የተነሣ እንደማይፈራ፥ ከድምፃቸውም የተነሣ እንደማይደነግጥ፥ እነርሱም ከቍጣው ብዛት የተነሣ ድል እንደሚሆኑና እንደሚደነግጡ፥ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።
በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፣ በቀኝና በግራ በዙሪያ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፣ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ በኢየሩሳሌም ትኖራለች።
አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እባርከዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፤ ከእስራኤልም ሰው ይነሣል፥ የሞዓብንም አለቆች ይመታል፤ የሤትንም ልጆች ሁሉ ይማርካል።
ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።