Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ናሆም 2:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አንበሳው ለልጆቹ የሚበቃውን ነጠቀ፥ ለእንስቶቹም ሰበረላቸው ዋሻውን በንጥቂያ፥ መደቡንም በቅሚያ ሞልቶታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አንበሳው ለግልገሎቹ የሚበቃውን ያህል ገደለ፤ ለእንስቶቹም ዐንቆ ገደለላቸው፤ የገደለውን በማረፊያ ቦታው፣ የነጠቀውንም በዋሻው ሞልቶታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አሁን ታድያ የአንበሶቹ ዋሻ፥ ደቦሎቻቸውን ያበሉበት፥ ወንዱና ሴቷ አንበሳ የሄዱበት፥ ግልገሎቹም ሳይፈሩ የተሰማሩበት ወዴት ነው?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አንበሳ ለግልገሎቹ የሚበቃቸውን ያኽል ዐድኖ አመጣ፤ ለእንስቲቱ አንበሳም የምትመገበውን ገድሎ አመጣላት፤ ዋሻውን በታደኑ እንስሶች ጒድጓዱንም በተቦጫጨቀ ሥጋ ሞላ።

Ver Capítulo Copiar




ናሆም 2:12
7 Referencias Cruzadas  

ኩሲ ደግሞ አለ፥ “በሜዳ እን​ዳ​ለች አራስ ድብና እንደ ተኳር የዱር እሪያ በል​ባ​ቸው መራ​ሮ​ችና ኀያ​ላን መሆ​ና​ቸ​ውን አባ​ት​ህ​ንና ሰዎ​ቹን ታው​ቃ​ለህ፤ አባ​ትህ አር​በኛ ነው፤ ሕዝ​ቡ​ንም አያ​ሰ​ና​ብ​ትም።


በፊቱ ካለው ብር​ሃን የተ​ነሣ ደመ​ና​ትና በረዶ የእ​ሳት ፍምም በፊቱ አለፉ።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በላኝ፤ ከፋ​ፈ​ለ​ኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደ​ረ​ገኝ፤ እንደ ዘን​ዶም ዋጠኝ፤ ከሚ​ጣ​ፍ​ጠ​ውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ።


የአንበሾችም መደብ፥ የአንበሾችም ደቦል የሚሰማራበት፥ አንበሳውና አንበሳይቱ ግልገሉም ሳይፈሩ የሚሄዱት ስፍራ ወዴት ነው?


እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰረገሎችዋንም አቃጥዬ አጤሳለሁ፥ ሰይፍም የአንበሳ ደቦሎችሽን ይበላቸዋል፣ ንጥቂያሽንም ከምድር አጠፋለሁ፥ የመልክተኞችሽን ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ አይሰማም።


እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ አን​በሳ ደቦል ያገ​ሣል፤ እንደ አን​በ​ሳም ይነ​ሣል፤ ያደ​ነ​ውን እስ​ኪ​በላ፥ የገ​ደ​ለ​ው​ንም ደሙን እስ​ኪ​ጠጣ አይ​ተ​ኛም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos