ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በክብርህ ላይ ውርደትን፥ በጌጥህ ላይም የሚነድና የሚያቃጥል እሳትን ይሰድዳል።
ዘኍል 21:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ወጣ፤ እስከ ሞዓብ ድረስ በላ፤ የአርኖን ሐውልቶችንም ዋጠ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እሳት ከሐሴቦን ወጣ፤ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ተንቦገቦገ፤ የሞዓብን ዔር፣ በአርኖን ከፍታዎች የሚኖሩትንም አለቆች በላ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ወጣ፤ የሞዓብን ዔር፥ የአርኖንን ተራራ አለቆች በላ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሐሴቦን እሳት ወጣ፤ ነበልባልም ከሲሖን ከተማ፥ የሞአብን ዔር አጠፋ የአርኖንንም ከፍተኛ ቦታዎች ደመሰሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሳት ከሐሴቦን፥ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ወጣ፤ የሞዓብን ዔር፥ የአርኖንን ተራራ አለቆች በላ፤ |
ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በክብርህ ላይ ውርደትን፥ በጌጥህ ላይም የሚነድና የሚያቃጥል እሳትን ይሰድዳል።
ለኀፍረት ይሆንብሃል፤ ሞዓብ በመሠዊያዎችዋ ደክማለችና፤ ለጸሎትም ወደ ጣዖቶችዋ ትሄዳለች፤ ሊያድኑአትም አይችሉም።
በራባ ቅጥር ላይ እሳትን አነድዳለሁ፤ በጦርነት ቀን በጩኸት መሠረቶችዋን ትበላለች፤ በፍጻሜዋም ቀን ትናወጣለች።
በሞዓብ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ የከተሞችዋንም መሠረቶች ትበላለች፤ ሞዓብም በድካምና በውካታ፥ በመለከትም ድምፅ ይሞታል፤
“እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ አሮኤርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ፤ በሰልፍም አትውጋቸው።
ዶግም ዛፎቹን፦ በእውነት እኔን በእናንተ ላይ ካነገሣችሁኝ እሳት ከዶግ ወጥቶ የሊባኖስን ዝግባ ካልበላው ከጥላዬ በታች ታርፉ ዘንድ ኑ አለቻቸው።
እንዲህ ባይሆን ግን ከአቤሜሌክ እሳት ትውጣ፤ የሰቂማንም ሰዎች፥ የመሐሎንንም ቤት ትብላ፤ ያም ባይሆን ከሰቂማ ሰዎች ከመሐሎንም ቤት እሳት ትውጣ፤ አቤሜሌክንም ትብላው።”