የእህላችንንም ቀዳምያት፥ የዛፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወይኑንና የዘይቱንም ፍሬ ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ ዐሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን ዐሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን።
ዘኍል 15:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጀመሪያ ከምታደርጉት ሊጥ አንድ እንጎቻ ለይታችሁ ቍርባን ታቀርባላችሁ፤ ከአውድማውም እንደምትለዩት ቍርባን እንዲሁ ትለያላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህንም ከመጀመሪያው ዱቄት ላይ ኅብስት ጋግራችሁ ከዐውድማ እንደ ተገኘ ቍርባን አድርጋችሁ አምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጀመሪያ ከምታዘጋጁት ሊጥ አንድ እንጐቻ ልዩ ስጦታ የሆነ ቁርባን አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ከአውድማውም እንደ ልዩ ስጦታ አድርጋችሁ እንደምታቀርቡት ቁርባን እንዲሁ ታቀርቡታላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸውም ከአዲስ እህል የተጋገረው የመጀመሪያው ኅብስት ለእግዚአብሔር ልዩ መባ ሆኖ ይቅረብ፤ ይህም ከምትወቁት እህል በማንሣት እንደምታመጡት ልዩ መባ በተመሳሳይ ይቅረብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጀመሪያ ከምታደርጉት ሊጥ አንድ እንጐቻ ለማንሣት ቍርባን ታቀርባላችሁ፤ ከአውድማም እንደምታነሡት ቍርባን እንዲሁ ታነሣላችሁ። |
የእህላችንንም ቀዳምያት፥ የዛፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወይኑንና የዘይቱንም ፍሬ ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ ዐሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን ዐሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን።
የመጀመሪያውን የምድርህን ፍሬ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወስዳለህ። ጠቦቱን በእናቱ ወተት አትቀቅል።”
የበኵራቱ ሁሉ መጀመሪያ ከየዓይነቱ፥ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል፤ በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የአዝመራችሁን ቀዳምያት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ።
እነዚህንም ዐሥራት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለበጎ መዓዛ በመሠዊያው ላይ አይቀርቡም።
“ከመጀመሪያው እህልህ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ብታቀርብ በእሳት የተጠበሰና የተፈተገ የእህል እሸት ታቀርባለህ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ መከሩንም ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤
ካህኑም ከበኵራቱ ኅብስት፥ ከሁለቱም ጠቦቶች ጋር በእግዚአብሔር ፊት ለቍርባን ያቅርበው፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ፈንታ ነው፤ ላቀረበው ለካህኑ ይሁን።
ለእግዚአብሔር ከሚሰጡት የፍሬ መጀመሪያ ከዘይትና ከወይን ከስንዴም የተመረጠውን ሁሉ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤
በዘመንህም ሁሉ አምላክህን እግዚአብሔርን መፍራትን ትማር ዘንድ፥ ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የእህልህን፥ የወይንህን፥ የዘይትህንም ዐሥራት፥ የላምህንና የበግህንም በኵራት ብላ።
ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።