ዘኍል 15:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእናንተና ከእናንተ ጋር ለሚኖር መጻተኛ አንድ ሕግና አንድ ፍርድ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእናንተም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖር መጻተኛ ይኸው ሕግና ሥርዐት እኩል ተፈጻሚነት ይኖረዋል።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእናንተና ከእናንተ ጋር ለሚቀመጥ መጻተኛ አንድ ዓይነት ሕግና አንድ ዓይነት ፍርድ ይኑራችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንኛውም ሕግና የሥርዓት መመሪያ ለሁላችሁም እኩል ነው።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእናንተና ከእናንተ ጋር ለሚቀመጥ መጻተኛ አንድ ሕግና አንድ ፍርድ ይሆናል። |
“ከሀገሩም ሕዝብ አንድ ሰው ኀጢአትን ሳያውቅ ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥራ ያለውን ትእዛዝ ቢተላለፍ፥ ቢበድልም፥
ባለማወቅ ነፍስ የገደለ ሁሉ ይሸሽባቸው ዘንድ እነዚህ ስድስት ከተሞች ለእስራኤል ልጆች፥ በመካከላቸውም ለሚቀመጡ እንግዶችና መጻተኞች መማፀኛ ይሆናሉ።
ወደ አገራችሁ መጻተኛ ቢመጣ፥ የእግዚአብሔርን ፋሲካ እንደ ፋሲካው ሕግ እንደ ትእዛዙም ያድርግ፤ ለመጻተኛና ለሀገር ልጅ አንድ ሥርዐት ይሁንላችሁ።”
የእስራኤልንም ሕዝብ አስቀድሞ ይባርኩአቸው ዘንድ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘ፥ እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ ጸሓፊዎቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ የሀገሩ ልጆችም፥ መጻተኞችም እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ አጠገብ፥ እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ አጠገብ ሆነው፥ የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ በተሸከሙት በሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በግራና በቀኝ ቆመው ነበር።