Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 4:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 “ከሀ​ገ​ሩም ሕዝብ አንድ ሰው ኀጢ​አ​ትን ሳያ​ውቅ ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥራ ያለ​ውን ትእ​ዛዝ ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢበ​ድ​ልም፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 “ ‘ከሕዝቡ መካከል አንዱ ሰው ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ከከለከላቸው ትእዛዞች አንዱን ተላልፎ ቢገኝ እርሱ በደለኛ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 “ከአገሩ ሕዝብም አንድ ሰው ባለማወቅ ጌታ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ተላልፎ ኃጢአት ቢሠራና ቢበድል፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 “ኃጢአት የሠራውና ባለማወቅም እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ካዘዛቸው ትእዛዞች አንዱን የተላለፈውና በደለኛ የሆነው ሰው ከተራው ሕዝብ ወገን ከሆነ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ከአገሩ ሕዝብም አንድ ሰው ኃጢአትን ሳያውቅ ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥራ ያለውን ትእዛዝ ቢተላለፍ፥ ቢበድልም፥

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 4:27
14 Referencias Cruzadas  

ለሀ​ገር ልጅ፥ በእ​ና​ንተ መካ​ከ​ልም ለሚ​ቀ​መጡ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል።”


በየ​በ​ዓ​ላ​ቱም፥ በየ​መ​ባ​ቻ​ውም፥ በየ​ሰ​ን​በ​ታ​ቱም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን መስ​ጠት በአ​ለ​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ እርሱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል።”


ከወ​ሩም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን እን​ዲሁ አድ​ርግ፤ ይኸ​ውም ስለ ሳተ​ውና ስለ በደ​ለው ሁሉ ነው። እን​ዲሁ ስለ ቤቱ አስ​ተ​ስ​ርዩ።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ቢስቱ፥ ነገ​ሩም ከማ​ኅ​በሩ ዐይን ቢሸ​ሸግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፉ፤


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ማና​ቸ​ውም ሰው ሳያ​ውቅ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥


“መኰ​ን​ንም ኀጢ​አ​ትን ቢሠራ፥ ሳያ​ው​ቅም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኩ፦ አት​ሥራ ያለ​ውን ትእ​ዛዝ ቢተ​ላ​ለፍ፥ እን​ዲ​ህም ቢበ​ድል፥


“ሰው ባለ​ማ​ወቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢታ​ወ​ቀው፥ ኀጢ​አት ስለ​ሆ​ነ​ች​በ​ትም ንስሓ ቢገባ፥


ከዚ​ህም በኋላ የሕ​ዝ​ቡን ቍር​ባን አቀ​ረበ፤ ስለ ሕዝቡ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሆ​ነ​ውን ፍየል ወስዶ አረ​ደው፤ አነ​ጻ​ውም፤ እንደ ፊተ​ኛ​ውም ለየው።


ለእ​ና​ን​ተና ከእ​ና​ንተ ጋር ለሚ​ኖር መጻ​ተኛ አንድ ሕግና አንድ ፍርድ ይሆ​ናል።”


“ብት​በ​ድ​ሉም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ህን ትእ​ዛ​ዛት ሁሉ ባታ​ደ​ርጉ፥


“አንድ ሰው ሳያ​ውቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ ስለ ኀጢ​አት አን​ዲት የአ​ንድ ዓመት እን​ስት ፍየል ያቀ​ር​ባል።


ትው​ልዱ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ቢሆን፥ ወይም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው የሚ​ኖር መጻ​ተኛ ቢሆን፥ ሳያ​ውቅ ኀጢ​አ​ትን ለሚ​ሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆ​ን​ለ​ታል።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወንድ ወይም ሴት ቸል ብለው ወይም ባለ​ማ​ወቅ ሰው ከሚ​ሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ የሠ​ሩት ቢኖር፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos