ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፤ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ፤ ለልጅ ልጃችሁም ሥርዐት ሆኖ ለዘለዓለም ታደርጉታላችሁ።
ዘኍል 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእናንተ፥ በእናንተም መካከል ለሚኖሩ መጻተኞች አንድ ሥርዐት ይሆናል፤ ለልጅ ልጃችሁም የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁ እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት መጻተኛ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማኅበረ ሰቡ ለእናንተም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖር መጻተኛ አንድ ዐይነት ደንብ ይኖረዋል፤ ይህም በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ የማይሻር ሥርዐት ነው። እናንተም ሆናችሁ መጻተኞቹ በእግዚአብሔር ፊት እኩል ትታያላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጥ መጻተኛ ለጉባኤው ሁሉ አንድ ዓይነት ሥርዓት ይኑር፥ ለልጅ ልጃችሁም የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁት መጻተኛውም በጌታ ፊት እንዲሁ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተም ሆናችሁ በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ እነዚህን የሥርዓት መመሪያዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መጠበቅ ይኖርባችኋል፤ እናንተም ሆናችሁ እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት አንድ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእናንተ በጉባኤው ላላችሁ በእናንተም መካከል ለሚቀመጥ መጻተኛ አንድ ሥርዓት ይሆናል፥ ለልጅ ልጃችሁም የዘላለም ሥርዓት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁ እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት መጻተኛ ይሆናል። |
ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፤ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ፤ ለልጅ ልጃችሁም ሥርዐት ሆኖ ለዘለዓለም ታደርጉታላችሁ።
እንዲሁም ኀጢአት እንዳይሆንባቸው፥ እንዳይሞቱም፥ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሲገቡ፥ በመቅደሱም ያገለግሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናል፤ ለእርሱ፥ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
መጻተኛም ከእናንተ ጋር ቢቀመጥ፥ ወይም በትውልዳችሁ መካከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ቍርባን በእሳት ቢያቀርብ እናንተ የምታደርጉትን እርሱ እንዲሁ ያደርጋል።
ትውልዱ በእስራኤል ልጆች መካከል ቢሆን፥ ወይም በመካከላቸው የሚኖር መጻተኛ ቢሆን፥ ሳያውቅ ኀጢአትን ለሚሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆንለታል።
እግዚአብሔርም አሮንን ተናገረው፤ እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ የለዩትን የመጀመሪያውን ቍርባኔን ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ፤ ለአንተ እስክታረጅ፥ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ የዘለዓለም ሕግ እንዲሆን ሰጥቼሃለሁ።
ወደ አገራችሁ መጻተኛ ቢመጣ፥ የእግዚአብሔርን ፋሲካ እንደ ፋሲካው ሕግ እንደ ትእዛዙም ያድርግ፤ ለመጻተኛና ለሀገር ልጅ አንድ ሥርዐት ይሁንላችሁ።”
በዚህም አይሁዳዊ፥ ወይም አረማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ናችሁና።
በእርሱ ዘንድ አይሁዳዊ፥ ግሪካዊም፥ የተገዘረ፥ ያልተገዘረም፥ አረመኔም፥ ባላገርም፥ ቤተ ሰብእና አሳዳሪ ማለት የለም ነገር ግን ክርስቶስ ለሁሉ በሁሉም ዘንድ ነው።
የእስራኤልንም ሕዝብ አስቀድሞ ይባርኩአቸው ዘንድ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ እንዳዘዘ፥ እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ ጸሓፊዎቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ የሀገሩ ልጆችም፥ መጻተኞችም እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ አጠገብ፥ እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ አጠገብ ሆነው፥ የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ በተሸከሙት በሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በግራና በቀኝ ቆመው ነበር።