ዘኍል 15:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጥ መጻተኛ ለጉባኤው ሁሉ አንድ ዓይነት ሥርዓት ይኑር፥ ለልጅ ልጃችሁም የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁት መጻተኛውም በጌታ ፊት እንዲሁ ይሆናል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ማኅበረ ሰቡ ለእናንተም ሆነ በመካከላችሁ ለሚኖር መጻተኛ አንድ ዐይነት ደንብ ይኖረዋል፤ ይህም በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ የማይሻር ሥርዐት ነው። እናንተም ሆናችሁ መጻተኞቹ በእግዚአብሔር ፊት እኩል ትታያላችሁ፤ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 እናንተም ሆናችሁ በመካከላችሁ የሚኖሩ መጻተኞች ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ እነዚህን የሥርዓት መመሪያዎች በተመሳሳይ ሁኔታ መጠበቅ ይኖርባችኋል፤ እናንተም ሆናችሁ እነርሱ በእግዚአብሔር ፊት አንድ ናችሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ለእናንተ፥ በእናንተም መካከል ለሚኖሩ መጻተኞች አንድ ሥርዐት ይሆናል፤ ለልጅ ልጃችሁም የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁ እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት መጻተኛ ይሆናል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ለእናንተ በጉባኤው ላላችሁ በእናንተም መካከል ለሚቀመጥ መጻተኛ አንድ ሥርዓት ይሆናል፥ ለልጅ ልጃችሁም የዘላለም ሥርዓት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁ እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት መጻተኛ ይሆናል። Ver Capítulo |