ዘኍል 13:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን ፥ “በኀይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱ ጋራ የወጡት ሰዎች ግን፣ “ከእኛ ይልቅ ብርቱዎች ስለ ሆኑ፣ ልናሸንፋቸው አንችልም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱ ጋር ወጥተው የነበሩት ሰዎች ግን፦ “ከእኛ ይልቅ እነርሱ ብርቱ ናቸውና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከካሌብ ጋር ሄደው የነበሩት ሰዎች ግን “እኛ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ከቶ ኀይል የለንም፤ በዚያ የሚኖሩት ሰዎች ከእኛ ይበልጥ ብርቱዎች ናቸው” ብለው ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን፦ በኃይል ከእኛ ይበረታሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም አሉ። |
ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድሪቱንም አዩአት፤ እግዚአብሔርም ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ የእስራኤልን ልጆች ልብ መለሱ።
ወዴት እንወጣለን? ሕዝቡ ታላቅና ብዙ ነው፤ ከእኛም ይጠነክራሉ፤ ከተሞቹም ታላላቆች፥ የተመሸጉም፥ እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፤ የረዐይትንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አስፈሩት።’
“እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ከአንተ የበለጡትንና የበረቱትን አሕዛብ፥ የቅጽራቸው ግንብ እስከ ሰማይ የሚደርስ ታላላቆች ከተሞችን ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገረዋለህ።
ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞች ግን የሕዝቡን ልብ አስካዱ፤ እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ እከተለው ዘንድ ተመለስሁ።
ሳኦልም ዳዊትን፥ “አንተ ገና ብላቴና ነህና፥ እርሱም ከብላቴንነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነውና ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመውጋት ትሄድ ዘንድ አትችልም” አለው።