Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 14:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከእኔ ጋር የወጡ ወን​ድ​ሞች ግን የሕ​ዝ​ቡን ልብ አስ​ካዱ፤ እኔ ግን አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሜ እከ​ተ​ለው ዘንድ ተመ​ለ​ስሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ዐብረውኝ ወደዚያ የወጡት ወንድሞቼ ግን፣ የሕዝቡ ልብ በፍርሀት እንዲቀልጥ አደረጉ፤ ሆኖም እኔ አምላኬን እግዚአብሔርን በፍጹም ልቤ ተከተልሁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ በፍርሃት አቀለጡ፤ እኔ ግን አምላኬን ጌታን ፈጽሜ ተከተልሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከእኔ ጋር ሄደው የነበሩ ሰዎች ግን የሕዝቡ ልብ በፍርሃት እንዲቀልጥ አደረጉ፤ እኔ ግን ለአምላኬ ለእግዚአብሔር በታማኝነት ታዛዥ ሆኛለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ አቀለጡ፥ እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ ተከተልሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 14:8
8 Referencias Cruzadas  

ከእ​ርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን ፥ “በኀ​ይል ከእኛ ይበ​ረ​ታ​ሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መው​ጣት አን​ች​ልም” አሉ።


ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ድም​ፃ​ቸ​ውን አን​ስ​ተው ጮኹ፤ ሕዝ​ቡም ሌሊ​ቱን ሁሉ አለ​ቀሱ።


ወዳጄ ካሌብ ግን ሌላ መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ ስለ ሆነና ስለ ተከ​ተ​ለኝ እርሱ ወደ ገባ​ባት ምድር አገ​ባ​ዋ​ለሁ፤ ዘሩም ይወ​ር​ሳ​ታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና ከእ​ነ​ዚህ፥ ልዩ ከሆነ ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌ​ብና ከነዌ ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር፤


ወዴት እን​ወ​ጣ​ለን? ሕዝቡ ታላ​ቅና ብዙ ነው፤ ከእ​ኛም ይጠ​ነ​ክ​ራሉ፤ ከተ​ሞ​ቹም ታላ​ላ​ቆች፥ የተ​መ​ሸ​ጉም፥ እስከ ሰማ​ይም የደ​ረሱ ናቸው፤ የረ​ዐ​ይ​ት​ንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየ​ና​ቸው ብለው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ልባ​ች​ንን አስ​ፈ​ሩት።’


ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌብ በስ​ተ​ቀር፥ እርሱ ግን ያያ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ተከ​ት​ሎ​አ​ልና የረ​ገ​ጣ​ትን ምድር ለእ​ርሱ፥ ለል​ጆ​ቹም እሰ​ጣ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈጽሞ ስለ ተከ​ተለ ኬብ​ሮን እስከ ዛሬ ለቄ​ኔ​ዛ​ዊው ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ ርስት ሆነች።


ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos