Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ሳሙኤል 17:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “አንተ ገና ብላ​ቴና ነህና፥ እር​ሱም ከብ​ላ​ቴ​ን​ነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነውና ይህን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ለመ​ው​ጋት ትሄድ ዘንድ አት​ች​ልም” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ሳኦልም መልሶ “አንተ ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነህ፣ ሰውየው ግን ከልጅነቱ ጀምሮ ውጊያ የተለማመደ ስለ ሆነ፣ ወጥተህ ይህን ፍልስጥኤማዊ ልትገጥመው አትችልም” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ሳኦልም መልሶ “አንተ ገና ልጅ ነህ፥ ሰውየው ግን ከልጅነቱ ጀምሮ ውጊያ የተለማመደ ስለሆነ፥ ወጥተህ ይህን ፍልስጥኤማዊ ልትገጥመው አትችልም” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ሳኦልም ዳዊትን፦ “አንተ ገና ልጅ ነህ፤ እርሱም ከልጅነቱ ጀምሮ ጦረኛ ስለ ሆነ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመውጋት ትሄድ ዘንድ አትችልም” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ሳኦልም ዳዊትን፦ አንተ ገና ብላቴና ነህና፥ እርሱም ከብላቴንነቱ ጀምሮ ጦረኛ ነውና ይህን ፍልስጥኤማዊ ለመውጋት ትሄድ ዘንድ አትችልም አለው።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 17:33
7 Referencias Cruzadas  

ከእ​ርሱ ጋር የወጡ ሰዎች ግን ፥ “በኀ​ይል ከእኛ ይበ​ረ​ታ​ሉና በዚህ ሕዝብ ላይ መው​ጣት አን​ች​ልም” አሉ።


ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።


አን​ተም የም​ታ​ው​ቃ​ቸው፥ ስለ እነ​ር​ሱም፦ በዔ​ናቅ ልጆች ፊት መቆም ማን ይች​ላል? ሲባል የሰ​ማ​ኸው ታላቅ፥ ብዙና ረዥም ሕዝብ የዔ​ናቅ ልጆች ናቸው።


አቤቱ፥ አድ​ነኝ፥ ደግ ሰው አል​ቆ​አ​ልና፥ ከሰው ልጆ​ችም መተ​ማ​መን ጐድ​ሎ​አ​ልና።


ንጉ​ሡም፥ “ይህ ብላ​ቴና የማን ልጅ እንደ ሆነ አንተ ጠይ​ቅና ዕወቅ” አለው።


ጎል​ያ​ድም ዳዊ​ትን ትኩር ብሎ አየው፤ ቀይ ብላ​ቴና፥ መል​ኩም ያማረ ነበ​ረና ናቀው።


ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን አለው፥ “እኔ ባሪ​ያህ የአ​ባ​ቴን በጎች ስጠ​ብቅ አን​በሳ ወይም ድብ ይመጣ ነበር፤ ከመ​ን​ጋ​ውም ጠቦት ይወ​ስድ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios